ሲዳማ ቡና መከላከያን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
አዲስ
አበባ ታህሳስ 25/2007
ዛሬ
በተካሄደው የ10ኛው
ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የእግር
ኳስ ጨዋታ ሲዳማ ቡና መከላከያን በማሸነፍ
መሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
ሲዳማ
ቡና ከመጀመሪያው ከዕረፍት በፊት ያገኘውን
የቅጣት ምት በቀጥታ ወደ ግብ በመለጥ 1
ለ
0 አሸንፏል።
ከጨዋታው
በኋላ አሰልጣኞች አስተያየታቸውን የሰጡ
ሲሆን የመከላከያው አሰልጣኝ ገብረመድህን
ኃይሌ "ሜዳውና
አንድ ስህተት ቀላል የማይባል ችግር ላይ
ጥሎናል፤ ዋጋም አስከፍሎናል"
ብሏል።
የሲዳማ
ቡናው አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው በበኩሉ
"የመልሶ
ማጥቃት አጨዋወት ስልትን ተግብረን ኳስን
ይዞ የሚጫወተውን መከላከያ አሸነፍን መውጣታችን
ትልቅ ውጤት ነው"
ሲል
በውጤቱ መደሰቱን ገልጿል።
አሰልጣኝ
ዘላለም "በቀጣይ
ዋንጫ ወደ ማንሳት እንድናነጣጠር አድርጎናል
ውጤቱ" በማለት
ውጤቱ የፈጠረለትን ተጨማሪ ተስፋ የገለጸው።
አሰልጣኙ
ይህን ያለው ጥቂት ልምድ ባላቸውና በበርካታ
ወጣቶች ስብስብ የተዋቀረው ቡድኑ ውጤታማ
ካደረገው በኋላ ነው።
"ጥሩ
ተፎካካሪ ሆኖ መጨረስ እንጂ ዋንጫን አላሰብነውም
ነበር አሁን ግን ይህን ማድርግ እንችላለን"
በማለትም
ቀጣይ ግቡን አመላክቷል።
ሁለቱም
አሰልጣኞች የመጫወቻ ሜዳው ውጤት ላይና
ተጨዋቾች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳለው
ገልጸዋል።
በአበበ
ቢቂላ ስታዲየም አራት የሚደርሱ ተጨዋቾች
ያለ ተቃራኒ ተጨዋች ንክኪ ሜዳው ባለው አስቸጋሪ
ተፈጥሮ ለጀርባ፣ ለጭንና ለባት ጡንቻ ጉዳት
ሲጋለጡ ተስተውለዋል።
ሜዳው
አስቸኳይ መፍትሄ የሚያሻው ቢሆንም በፍጥነት
ግን መፍታት እንደማይቻል ነው ከፌዴሬሽኑ
የተገኘ መረጃ ያመላከተው።
ብሔራዊ
ስታዲየሙ 12ኛውን
የአፍሪካ ወጣቶች የአትሌቲክስ ሻምፒዮናን
ከማስተናገድ ጋር ተያይዞ እድሳት ላይ በመሆኑ
ነው ውድድሩ ወደ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እንዲዛወር
የተደረገው።
ፕሪሚዬር
ሊጉ ነገ በአበበ ቢቂላ ስታዲዮምና በክልል
ከተሞች ቀጥሎ ይካሄዳል።
-
See more at:
http://www.ena.gov.et/index.php/sport/item/926-2015-01-04-04-51-22#sthash.qAOmWhuF.dpuf
Comments
Post a Comment