በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ቅናሽ ተደረገ

የንግድ ሚኒስቴር በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቋል ።
የዋጋ ቅናሽ ማሰተካከያ የተደረገው የነዳጅ ምርቶች የአለም ገበያ ዋጋ እየቀነሰ መምጣቱን መነሻ በማድረግ መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲነግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ያስታወቀው ።
በዚህም መሰረት ከነገ ጥር 23 እስከ የካቲት 30፣ ቀን 2007 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የነደጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን ይፋ አድርጓል ።
በዋጋ ክለሳውም ቤንዚን ኢታኖል ድብልቅ በሊትር 17 ብር ከ20 ሳንቲም ፣ ነጭ ናፍታ 16 ብር ከ10 ሳንቲም ፣ ኬሮሲን 14 ብር ከ42 ሳንቲም ፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 13 ብር ከ91 ሳንቲም ፣ እንደዚሁም ከባድ ጥቁር ናፍታ 13 ብር ከ23 ሳንቲም ሲሆን፥ የአውሮፕላን ነዳጅ ደግሞ 15 ብር ከ21 ሳንቲም በሊትር የሚሸጥ ይሆናል ።
ሚኒስቴሩ የነዳጅ ምርቶቹን ዋጋ በዝርዝር በነገው እለት በጋዜጣ የሚያወጣ መሆኑንና በሁሉም የሃገሪቱ ክፍል ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑንም አስታውቋል ።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር