POWr Social Media Icons

Wednesday, October 22, 2014በሃዋሳ እና በሌሎች ከተሞች የተገነቡ የቡና ቅምሻና ጨረታ ማዕከላት የቡና ግብይት ስርዓቱ ላይ ይታይ የነበረውን ችግር በማስቀረት ግብይቱ ግልጽ አስተማማኝና ቀልጣፋ እንዲሆን ኣስችለዋል መባሉ ተሰምቷል፤ ከክልሉ በተያዘው ዓመት ከ134 ሺህ ቶን የሚበልጥ የታጠበና ደረቅ ቡና ለገበያ ይቀርባል እየተባለ ነው። ወሬው የኢዜኣ ነው፦
ከደቡብ ክልል ለገበያ የሚቀርበውን የቡና መጠን በጥራት በመጨመር የሀገሪቱን የውጪ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ አስታወቀ፡፡
በቢሮው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ባለቤት አቶ መላኩ እንዳለ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ከክልሉ በተያዘው ዓመት ከ134 ሺህ ቶን የሚበልጥ የታጠበና ደረቅ ቡና ለገበያ ይቀርባል።
ክልሉ ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና ማምረት የሚችል ቢሆንም ህገወጥ የቡና ግብይትና ዝውውር በገበያው ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ለውጪ ምንዛሪ መጠን ማነስ ምክንያት ሆኖ መቆየቱን ጠቁመዋል።
ህገወጥ የቡና ዝውውርና ግብይትን ለማስቀረትና በግብይት ስርዓቱ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት ለውጪ ገበያ የሚቀርበውን ቡና ጥራት ለማስጠበቅ የቡና ግብይት ደንብና መመሪያ ተዘጋጅቶ ግባራዊ መሆኑን ገልጸዋል።
የቡና ግብይት ስርዓቱ እሴት በማይጨምሩ ደላሎችና ህገወጥ የቡና አዘዋዋሪዎች እጅ የወደቀ በመሆኑ አምራቹ ለምርቱ ተመጣጣኝ ዋጋ እንደማያገኝ ገልጸው በቡናው ላይ የጥራት መጓደል ችግር የሚፈጠር በመሆኑ የሚፈለገውን ያህል ገቢ ማግኘት እንዳልተቻለ ተናግረዋል፡፡
የቡና ግብይት ስርዓቱ ግልጽና የአምራቹን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲያስችል የገበያ መሰረተ ልማት የማስፋፋት ስራ መከናወኑን ገልጸው ባለፉት አራት ዓመታት አንድ ሺህ 618 የመጀመሪያ ደረጃ የቡና ግብይት ማዕከላት በማቋቋም ሕጋዊ ነጋዴዎች ፈቃድ በመያዝ እንዲሰሩ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ የቡና ግብይት ማዕከላት ለአርሶ አደሩና ለግብይት ተሳታፊዎች ከሚሰጡት ጥቅም ባሻገር የቡና ጥራትን ለማስጠበቅና ህገወጥ የቡና ንግድና ዝውውርን ለመቆጣጠር አስችሏል ብለዋል፡፡
በሀዋሳ ፣ዲላ ፣ወላይታ ሶዶና ቦንጋ ከተሞች የተገነቡ የቡና ቅምሻና ጨረታ ማዕከላት ስራ በመጀመራቸው የቡና ግብይት ስርዓቱ ላይ ይታይ የነበረውን ችግር በማስቀረት ግብይቱ ግልጽ አስተማማኝና ቀልጣፋ እንዲሆን ማስቻሉን አስታውቀዋል፡፡
ከክልሉ በያዝነው አመት ለውጪ ገበያ የሚቀርበው የቡና መጠን ካለፈው አመት በመጨመር የውጪ ምንዛሪ መጠንን ለማሳደግ ለግብርና ባለሙያዎች አርሶ አደሮችና ለግብይት ስርዓቱ ተሳታፊ ለሆኑ አካላት ስልጠና መሰጠቱን ጠቁመዋል፡፡
በያዝነው አመት በማህበራትና በግል ለገበያ የሚቀርበው የታጠበና ደረቅ ቡና ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር ከ43 ሺህ ቶን በላይ ብልጫ እንዳለው አቶ መላኩ አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜኣ

የጋራ ምክር ቤቱ በታላላቅ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከገዥው ፓርቲ ጋር በሰከነ መንፈስ ለመወያየትና ችግሮችን ለመፍታት እድል ፈጥሯል-ፓርቲዎች

አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ በታላላቅ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ከገዥው ፓርቲ ጋር በጋራ ለመስራትና በመካከላቸው የሚከሰቱ ቅሬታዎችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እድል መፍጠሩን አንዳንድ አባል ፓርቲዎች ገለፁ።
በጋራ ምክር ቤቱ ያልተካተቱ ፓርቲዎችም በአገሪቱ የተጀመረው የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እንዲጠናከር የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ ቀርቧል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ካነጋገራቸው የጋራ ምክር ቤቱ አባል ፓርቲዎች መካከል የአዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ) ፕሬዝዳንት አቶ አስፋው ጌታቸው ከገዥው ፓርቲ ጋር የሚደረገው ውይይት በታላላቅ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በፓርቲዎች መካከል መግባባትን ከመፍጠር ባለፈ የመጪውን ትውልድ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ለማዳበር የጎላ ሚና አለው ብለዋል።
ፓርቲዎች በአንድ አገራዊ ጉዳይ ላይ የሰከነ ውይይት ማድረጋቸው በመካከላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶችን በቀላሉ እልባት ከመስጠቱም ባሻገር ለመደብለ ፓርቲ የፖለቲካ ስርዓቱ መጠናከር የማይተካ ድርሻ አለው።
በምክር ቤቱ ውስጥም የሁሉም አባል ፖለቲካ ፓርቲዎች አገራዊና ድርጅታዊ አጀንዳዎች እንደሚስተናገዱ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ ጠንካራ ክርክሮችን በማድረግ ለህዝብ የሚቀርቡ አማራጭ ሃሳቦች ጎልተው እንዲወጡ ይደረጋል ብለዋል።
አቶ አስፋው እንዳሉት እስከታችኛው የስልጣን እርከን ድረስ የምክር ቤቱ አባላት ለሚያነሷቸው ችግሮች ከሁሉም ፓርቲዎች የተውጣጡ አጣሪ ኮሚቴዎችን በማዋቀር ዘላቂ እልባት እንዲኖር እድል መስጠቱንም ጠቅሰዋል።
በጋራ ምክር ቤቱ የተቋቋመው ኮሚቴ በተከሰቱ ችግሮች ዙሪያ የሚያቀርበው ሪፖርት በመነሳት ገዥው ፓርቲ ስህተት ፈጽሞ ከሆነ ሂስ እንዲወስድና በቀጣይ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ይደረጋል።
ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ያልተጨበጠ ውንጀላና ክስ እያቀረቡ ከሆነ እንዲስተካከሉ ጠንካራ ሂስ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
"ፓርቲዎች በጋራ ምክር ቤቱ መወያየታቸው በአገሪቱ ብቸኛው አማራጭ ሰላማዊ ትግል ብቻ መሆኑን የሚያስተምር መድረክ ነው" ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ፍትህና ዴሞክራሲ ብሄራዊ ግንባር (ኢፍዴብግ) ዋና ፀሐፊ አቶ ግርማዬ ሓደራ ናቸው።
"ችግሮችን ከገዥው ፓርቲ ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብሎ በመነጋገር ለመፍታት መጣር የዴሞክራሲ ስርዓት ትልቁ መለኪያ ከመሆኑም ባሻገር ፓርቲዎች ለሰላማዊ ትግሉ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል" ሲሉም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ህዝቦች አቭዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር(ኢህአዴግ) የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደስታ ተስፋው በበኩላቸው የጋራ ምክር ቤቱ ፓርቲዎች የያዙትን አጠቃላይ ፕሮግራም በማንፀባረቅ በጋራ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ አማራጭ ሃሳቦችን እንዲያቀርቡ እድል ከመፍጠሩ ባሻገር በአገሪቱ የሚካሄደው ምርጫ ነፃ፣ፍትሃዊና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅም የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለዋል።
ተቃዋሚ ፓርቲዎችም  ገዥው ፓርቲ በአገራዊ ጉዳዮች ላይ አላወያየንም ብሎ በጭፍን ከመተቸት ይልቅ የስነ-ምግባር ደንቡን ፈርመው ወደ ጋራ ምክር ቤቱ በመግባት ለሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ትግሉ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።
"በጋራ ምክር ቤቱ ውስጥ ገብተው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ትግል ለማካሄድ ፍላጎት ካላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመስራት ኢህአዴግ ሁልጊዜም ዝግጁ ነው"ሲሉም አቶ ደስታ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ፕሬዝዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ እንደተናገሩት ደግሞ ፓርቲዎች በጋራ ምክር ቤቱ መወያየታቸው በመካከላቸው የእኩልነት መንፈስ እንዲፈጠር ከማድረጉ ባለፈ በአገራዊ ጉዳዮች ላይ የተሻለ መግባባትን እየፈጠረ ይገኛል።
"የጋራ ምክር ቤቱ የውስጥ ዴሞክራሲን በማሳደግ አገራዊና ህዝባዊ አጀንዳዎችን ለማንሽራሸር ትልቅ ሚና አለው" ያሉት አቶ ተሻለ በስነ-ምግባር ደንብ አዋጁ ለፓርቲዎች የተሰጠውን መብት አሟጦ ለመጠቀም በቅንነትና በግልጽ መወያየቱ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል።
በምክር ቤቱ አባል ያልሆኑ ሌሎች ፓርቲዎችም ልዩነት በማይፈጥሩ ጉዳዮች ላይ ወደአለመግባባትን ከመሄድ ይልቅ ህግ ሆኖ እያገለገለ ያለውን የስነ-ምግባር ደንብ ፈርመው ወደ ጋራ ምክር ቤቱ እንዲቀላቀሉ ጠይቀዋል።
የጋራ ምክር ቤት አባል ፓርቲዎችም “ምክንያታዊና አሳማኝ በሆኑ ጉዳዮች ያለፍርሃት ያለስጋት በቅንነት ስለእውነት ስንል የዴሞክራሲ  ባህሪያት የሚጠይቁንን ሁሉ እያደረግን እንገኛለን።”ሲሉ ተናግረዋል።
የምርጫ ስነ-ምግባር ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 662/2002 አንቀጽ 20 ንዑስ አንቀጽ አንድ መሰረት በምርጫው ሂደት የሚነሱ የአፈፃፀም፣የዴሞክራሲ፣የሰብዓዊ መብትና የህግ የበላይነትን በኢትዮጵያ ለማጎልበት በተከታታይ እየተገናኙ እንዲወያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት እንዲያቋቁሙ መብት ተሰጥቷቸዋል።
በዚህም መሰረት ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ ዘጠኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ አባል ሆነው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።
ምንጭ፦ ኢዜኣ

8th Bi-Annual Microfinance Conference

22.10.2014 - 24.10.2014, Hawassa, Ethiopia
Inclusive Finance for Expanding Opportunities to the Financially Excluded Population
This conference aims to share good practices and innovative ideas in Microfinance, by providing participants with a forum to exchange ideas aimed at contributing to the development of the microfinance industry and financial cooperatives, and to further strengthening the policy at a national level. Topics will include:
  • Savings mobilization of MFIs;
  • Financial inclusion;
  • SACCOs development and their role in promoting financial inclusion;
  • Value chain financing and MFIs; and
  • Agricultural finance, amongst others.
For more information, please visit the 8th Bi-Annual Microfinance Conference website.
Source: http://www.mfw4a.org/events/event-details/article/2/8th-bi-annual-microfinance-conference.html
Djibouti internet start-up to boost broadband

Internet access in east Africa is still relatively slow and costly but a Djibouti-based technology start-up company has ambitions to help change that.

Djibouti Data Centre (DDC), set up by a group of local and international investors 18 months ago, is the first data centre and internet exchange in east Africa connected to eight fibre optic cables that are part of the main internet route from Europe to Asia.

The internet route travels through the Mediterranean, Red Sea and into the Indian Ocean, passing by tiny Djibouti, which is sandwiched between Eritrea, Somalia and Ethiopia.

African internet users have typically enjoyed little benefit from these cables passing along its coast because connectivity to them has been limited, something the DDC aims to correct as it plans to expand from its home base into Kenya, Ethiopia, South Sudan and Somalia, which are all at varying stages of internet development.

“The Djibouti market itself may be small, but the DDC serves as a unique gateway hub to the many millions of customers in these neighbouring east Africa countries,” Anthony Voscarides, chief executive of Djibouti Data Centre, said.

The company launched services in March 2013 in partnership with Djibouti Telecom.

It hopes to connect to at least three more cables on the Europe/Asia route next year.

“Africa has historically been challenged by high internet costs,” Voscarides, an Australian former telecoms industry executive, said.

According to The Internet Society, 15.7% of Kenya’s average GDP per capita is required for broadband access, compared to 6.1% in South Africa and less than 2% in most of Europe.

In Ethiopia the figure rises to 60.4% while in Uganda it is 31% and 7.4% in Sudan.

Less than 2% of Ethiopia’s 97 million population use the internet.

But Sydney-based consultants BuddeComm said the country’s “broadband market is set for a boom following massive improvements in international bandwidth, national fibre backbone infrastructure and 3G mobile broadband services”.

Kenya is the biggest market in the region with internet penetration of 39%, the fourth-highest in Africa, according to the International Telecommunications Union.

In terms of median download speeds, however, Kenya is ranked 105th globally, while Ethiopia is 94th, Sudan 154th and South Africa is 116th, according to the Internet Society.

Madagascar is the highest ranked African country at 61. The DDC’s goal is to expand into neighbouring east African countries with small data centres which would then allow telecom operators, cable companies and others in those countries to access the submarine cables off Djibouti via its main datacentre. 

Source: www.thenewage.co.za
Photo: en.alkuwaityah.com
Doctors without Borders transferring successfully its Mother and Child Project in Ethiopia

Doctors without Borders (MSF) announced the beginning of transferring the successful Mother and Child Healthcare project in Sidama Zone to the Ministry of Health at the end of this month, Ethiopian News Agency (ENA) reported.

The philanthropist group has been implementing a Mother and Child Healthcare project providing free medical service for mothers and children in Aroressa and Chire Woredas of Sidama Zone, SNNP regional state, since 2012, the MSF released reported.

The MSF have been providing consultations for at least 12027 prenatal and postnatal cases as well as over 2,000 deliveries registered since the initiation of the intervention. 


በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕ/ ሊግ ውድድር መጪው እሁድ ጥቅምት 16፣2007 የሲዳማ ቡና ከሙገር ሲሚንቶ በይርጋለም ስታድዬም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ የምጋጠሙ ሲሆን፤ ሌላው የሲዳማ ክለብ የሆነው ሃዋሳ ሲቲ  በተመሳሳይ ቀን እና ሰዓት በመዳው ኣርባምንጭ ከነማን ይገጥማል።  ለሁለቱም የሲዳማ ክለቦች መልካም እድል ወራንቻ ብሎግ ይመኛል።
Rhythmic drum beats echoed for blocks, and tantalizing smells of made-to-order dumplings and freshly stuffed pupusas welcomed guests to the sixth annual World of Montgomery Festival on Sunday.
Westfield Wheaton’s parking lot was transformed into a brilliantly colored display of cultural diversity. Thousands enjoyed the free event showcasing Montgomery County’s rich diversity.
The festival was sponsored by Fund for Montgomery and organized by KID (Kids International Discovery) Museum. The museum, which will have a grand opening on Sunday in Bethesda, led many hands-on, kid-friendly activities, such as making, decorating, and flying kites. Parents joined children in directing newly made kites through the windy weekend sky.
The museum also organized a festival passport for children, with a scavenger hunt, fun facts about cultures, and a spot for stamps from each country’s booth.
“I love this event,” said Amanda West, a mother of two from Silver Spring. “My kids interact with these cultures every day, but this is a great chance for them to really learn about it. Now my 4-year-old wants to go to China and meet the pandas.”
The festival featured exhibits representing the four largest immigrant populations in Montgomery County: China, El Salvador, Ethiopia, and India. Each exhibit was filled with artifacts and clothing, and had hands-on experiences for children.
The Chinese tent had lessons on drawing Chinese characters and the ancient art of paper cutting. There were other traditional Chinese activities, such as organizing brightly colored plastic shapes to create a picture. A few talented Chinese artists drew flowers and panda bears on T-shirts and gave them to guests.
The El Salvadorian tent had lessons for children on making a “capirucho” game. Guests tied string to a wooden ball, fastened the string through a hole in a foam cup, and practiced flinging the ball in the air, so it would land in the cup.
The Ethiopian tent was popular on the cool blustery fall day, as guests warmed up while experiencing a traditional coffee ceremony. Guests breathed in the aroma of brewed coffee, which was poured continuously into many small cups on an ornate trey and offered to guests.
At the Ethiopian exhibit, children learned how to make pinwheels and write their names in Amharic, Ethiopia’s official language.
In the Indian tent, visitors tried on saris and turbans, and played authentic Indian instruments, including the sitar, the sarod, and the sarangi.
People decorated clothes using traditional Indian dyes. Guests received white T-shirts and the opportunity to turn them into a variety of vibrant colors.
Each country was represented by at least one food station. The Dumpling Dojo had chicken and shrimp dumplings in bacon. Los Cobanos offered meat and veggie tacquitos. The Taste of Meski food truck tossed traditional Ethiopian salads, and Tandoori Nights grilled chicken and rice.
Performances at either end of the festival ranged from dancers on stilts to children dancing with swords.
The entire festival paused as volunteers left their booths to watch and participate in a parade. Groups danced and marched their way around the festival grounds and interacted with any audience members who would let them.
“I loved the parade. I danced with the drums and a giant,” said 3-year-old Juan-Pablo Herrera, referring to a man on stilts. “I can’t wait to come back next year.”
ምንጭ፦ www.gazette.net
‹‹ፈንዱ የተቋረጠው ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር በተገናኘ አይደለም›› ዲኤፍአይዲ
በእንግሊዝ መንግሥት ገንዘብ ለኢትዮጵያ የደኅንነት ኃላፊዎች ይሰጥ የነበረው የደኅንነት ማኔጅመንት ፕሮግራም ተቋረጠ፡፡
ሪፕሪቭ የተባለ ነፃ የሕግ አገልግሎት የሚሰጥ የእንግሊዝ ኩባንያና ሌሎች የሰብዓዊ መብት አቀንቃኞች፣ ካለፈው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ የእንግሊዝ መንግሥት ይህንን ፕሮግራም እንዲያቋርጥ ግፊት ሲያደርጉ ነበር፡፡ 
እነዚህ ወገኖች ይህንን ግፊት የጀመሩት የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ምክንያት ዜጐችን ከመኖሪያ አካባቢያቸው ያፈናቅላል በሚል ክስ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የግንቦት ሰባት ጸሐፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመንና በኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች፣ ባለፈው ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ ኤርትራ ለመጓዝ የመን ሰንአ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር ውለው ወዲያውኑ ለኢትዮጵያ መንግሥት ከተላለፉ በኋላ፣ በእንግሊዝ መንግሥት ላይ ጫናው እንዲጠናከር ሲጥሩ ነበር፡፡
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ መንግሥት በኃይልም ሆነ በተገኘው አማራጭ ለመለወጥ የሚታገለው የግንቦት ሰባት አመራር ይሁኑ እንጂ፣ ዜግነታቸው እንግሊዛዊ መሆኑ ተጨማሪ ግፊት ይፈጥራል ብለውም ነበር፡፡
እሳቸው በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ በእንግሊዝ መንግሥት ላይም ሆነ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ከፍተኛ ግፊት ከሚያደርጉት መካከል፣ መቀመጫውን ለንደን ያደረገው ነፃ የሕግ አገልግሎት የሚሰጠው ተቋም የሆነው ሪፕሪቭና የአውሮፓ ኅብረት የሰብዓዊ መብት ኮሚቴ ይገኙበታል፡፡
የሪፕሪቭ የሕግ ዳይሬክተር ቲኔክ ሀሪስ በነሐሴ ወር ለእንግሊዝ መንግሥት ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ጀስቲገን ግሪንግ በጻፉት ደብዳቤ፣ ‹‹የእንግሊዝ ዜግነት ያለውን ግለሰብ ላገተውና ቶርቸር በማድረግ ለሚጠረጠረው የኢትዮጵያ መንግሥት ኃላፊዎች ይህንን ፕሮግራም መስጠት ተገቢ ነው ወይ? ተገቢ ነው ብለው ካላመኑ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስካልተፈቱ ድረስ ምን ዕርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ ቢያሳውቁን?›› በማለት ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡
የአውሮፓ ኅብረት የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኮሚቴ ባለፈው መስከረም ወር ባካሄደው ጉባዔው በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስር ላይ የእንግሊዝ መንግሥት ምንም ዓይነት ጫና አለማሳደሩን በመውቀስ አስፈላጊ ነው የተባለ ውሳኔ በኢትዮጵያ ላይ ለማሳለፍ የሁለት ወራት ጊዜ ቀጠሮ ወስዶ መበታተኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ይህ ጫና ባለበት በአሁኑ ወቅት የእንግሊዝ መንግሥት ዲፓርትመንት ፎር ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት (ዲኤፍአይዲ) ለኢትዮጵያ የደኅንነት ኃላፊዎች ይሰጥ የነበረውን የደኅንነት ማኔጅመንት ፕሮግራም አቋርጧል፡፡ 
ፕሮግራሙ የተመረጡ የኢትዮጵያ የደኅንነት ኃላፊዎች በእንግሊዝ አገር በደኅንነት ማኔጅመንት የማስትሬት ዲግሪያቸውን እንዲሠሩ የሚያግዝ ነበር፡፡ 
የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ ወደ 70 ሚሊዮን ፓውንድ ሲሆን፣ ለመጀመሪያው ዙር ፕሮግራም ሁለት ሚሊዮን ፓውንድ ያስፈልግ ነበር፡፡ 
ለዚህ ዓመት ተይዞ የነበረው የሁለት ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ለአጠቃላይ ፕሮግራሙ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
የዲኤፍአይዲ የኢትዮጵያ ቢሮ ጉዳዩን በተመለከተ ከሪፖርተር በኢሜይል ለቀረበለት ጥያቄ ፕሮግራሙ መቋረጡን አረጋግጧል፡፡ ነገር ግን ምክንያቱ ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር ግንኙነት እንደሌለው አስታውቋል፡፡ 
‹‹ፕሮግራሙ የተቋረጠው የእንግሊዝ መንግሥት ለፕሮግራሙ የሚያወጣውና የሚያገኘው ምላሽ (ኢንቨስትመንት ሪተርን) የሚጣጣሙ ባለመሆናቸው ነው፤›› በማለት በደፈናው መልሷል፡፡