POWr Social Media Icons

Tuesday, August 5, 2014በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በሲዳማ ዞን ኣዳዲስ የተሽከርካሪ ስምርት መስመር መከፈቱን የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ  ገለጸ።

የቢሮውን ኃላፊ አቶ ላጫ ጋሩማ ጠቅሶ ኢዜአ እንደዘጋበው፤ በዞኑ 21 ኣዲስ የሰምሪት መስመር ከፍቷል።


አዲስ በተከፈቱ የስምሪት መስመሮች ቋሚ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን በመመደብና ታሪፍ በማውጣት የትራንስፖርት አገልግሎት ሳይቆራረጥ እንዲቀጥል መደረጉንና በዚህም አርሶ አደሩ ምርቱን ገበያ ለማቅረብና በእግር ረዥም መንገድ ከመጓዝ እንዳላቀቀው እኙሁ ኃላፊ ተናግረዋል።

በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ የዶሬ ባፈና ነዋሪ አርሶ አደር ብርሀኑ ባጢሶና አርሶ አደር ይፍሩ ይማም ቀደም ሲል ከሀዋሳ እስከ ወረዳ ከተማ  ካልሆነ ወደ ገጠር ቀበሌ ለመጓዝ የፈረስ ጋሪና የጭነት መኪና ይጠቀሙ እንደነበር አስታውሰው አሁን በሳምንቱ አብዛኛው ቀናት መለስተኛ አውቶብሶች በበመደባቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።