POWr Social Media Icons

Monday, August 4, 2014በቃጠሎ  ከወደሙ ቤቶች መካከል

በቃጠሎ  ከወደሙ ቤቶች መካከል

በቃጠሎ  ከወደሙ ቤቶች መካከል

  • 46 ቤቶች ከእነ ንብረታቸው በቃጠሎ ወድሟል፤
  • 400 የሲዳማ ብሄር ተወላጆች ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸው ከኣከባቢው እንዲሰደዱ በመደረጋቸው ከ2 ወራት በላይ በጫካና በዱር እየተንገላቱ ነው

በኦሮሚያ ክልል በባሌ ሮቤ ዞን በሀንጌቱ ወረዳ ለኣመታት ከኣከባቢው ህዝብ ጋር ተጋብቶ ተዋልዶ በሰላም የኖሩት የሲዳማ ብሔር ተወላጆች በወረዳው ኣስተዳደር ቤት ንብረታቸውን ተቀምተው ከኣከባቢው እንድለቁ በመደረግ ላይ ናቸው።

ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ከሃዋሳ የላከልክ ዘጋባ እንደሚያመለክተው ከሆነ፤ በወረዳው ኣስተዳዳር የተመራው የጸጥታ ኃይል በኣንድ ቀን ብቻ46 ቤቶች ከእነ ንብረታቸው በማቃጠል፣በ400 ሰዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ በመፈጸም ለዘመናት ከኖሩበት አካባቢ እንድሰደዱ እና ከ2 ወራት በላይ በጫካና በዱር እንድገላቱ ኣድርጓል።

400 በላይ በደል የደረሰባቸው የሲዳማ ተወላጆች በተወካዮቻቸው የደረሰባቸውን ኢሰብኣዊ ድርጊት በመቃዎም ብሎም በደ እንዲቆምና በደል የፈፀሙ አካላት በህግ እንዲጠየቁ ተፈናቃዮች ለፌዴራል ጉዳይ ሚንስቴር አቤቱታ ቢያቀርቡም አቤቱታውን የተቀበለ አካል ጉዳዩ እንዲጣራ ለኦሮሚያ ክልል መንግስት በስልክ ትዕዛዝ ሠትተናልና ሄዳችው የሚሰጣችሁን መልስ ጠብቁ የምል ምላሽ መሰጠቱ ታውቋል፡፡

ሆኖም እስከ ዛሬ ድረሰ ምንም መፍትሄ ሳይሰጥ ተጨማሪ ነዋሪዎች ላይ ንብረት የማውደምና የማፈናቀል እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የተፈናቃዮችን አቤቱታ ተቀብሎ ለባሌ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤትና ለሀረና ቡሉቅ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ጉዳዩ እንዲጣራ በቁጥር ሰመኮ/21/106/06 በቀን 09/11/2006 /ም ደብዳቤ የጻፈ ቢሆንም፤ እስከ ኣሁን ድረሰ ምላሽ ካለመስጠታቸው የተነሳ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሴቶችና ህጻናት መጠለያ ኣጥተው በመሰቃየት ላይ ናቸው፡፡

በጉዳዩ ላይ የሲዳማ ዞን መንግስት እስከ ኣሁን ድረሰ ይህ ነው የምባል እርምጃ ኣለመውሰዱ ታውቋል።

ኣዲስ

በቡሉቅ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ የሲዳማ ብሔር ተወላጆች ለተለያዩ የመንግስት ኣካላት ያቀረቡት ኣቤቶታና የተሰጣቸው ምላሽ.pdf