Posts

Showing posts from May, 2014

የቡና ፈቃድ ኖሯቸው ኤክስፖርት አድርገው የማያውቁ 37 ነጋዴዎች ፈቃድ ተሰረዘ

- ለኤክስፖርት የተዘጋጀ ቡና ላይ የኮንትሮባንድ ንግድ ደርቷል በቡና ንግድ ተሳታፊ ሳይሆኑ የቡና ፈቃድ አውጥተው ለዓመታት የተቀመጡና ምናልባትም አጭበርባሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉ 37 ግለሰቦችን ፈቃድ መሰረዙን የንግድ ሚኒስትሩ አስታወቁ፡፡ የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ የአሥር ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ሲያቀርቡ፣ የቡና ንግድ መቀዝቀዙንና ኮንትሮባንድ መስፋፋቱን፣ እንዲሁም ከቡና ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት የንግድ ሚኒስቴር ምን እያደረገ እንደሆነ ተጠይቀዋል፡፡ የቡና ጉዳይ ድሮ በሚኒስቴር ደረጃ ይመራ ከነበረበት ወርዶ በአንድ ተቋም ውስጥ መመሸቁ እንደሚያሳስባቸው የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ከኮንትሮባንድ መስፋፋት በተጨማሪ የቡና ንግድ ሳይኖራቸው የቡና ፈቃድ ያወጡ መኖራቸውን አስረድተዋል፡፡ በቡና ንግድ ካልተሰማሩ ፈቃዱን ለምን እንደሚፈልጉት መገመት እንደሚቻል የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ዋነኛው መንግሥት ለቡና ንግድ የሚሰጠውን ትኩረትና ጥቅማ ጥቅም ለመቀራመት ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡ በቡና ንግድ ዘርፍ ለሚሰማሩ መንግሥት ቅድሚያ የባንክ ብድርና የውጭ ምንዛሪ እንዲያገኙ ስለሚያደረግ፣ እነዚህ በቡና ንግድ ላይ ለመሰማራት ፈቃድ ያወጡ ነገር ግን ኤክስፖርት አድርገው የማያውቁ ነጋዴዎች ይህንን ጥቅም ለመመዝበር አቅደው ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡ ‹‹እንዲህ ዓይነት የማጭበርበር ሥራ የሚሠሩ የቡና ንግድ ፈቃድ ይዘው የተቀመጡ ነጋዴዎች ፈቃድ ተሰርዟል፤›› ብለዋል፡፡ እነዚህ ነጋዴዎች የሚያገኙትን ብድር ተጠቅመው አራጣ የማበደር ተግባር ውስጥ  ተሰማርተው ሊሆኑ ይችላል የሚሉት አቶ ከበደ፣ የነጋዴዎቹን ማንነት ከመግለጽና ፈቃዳቸውን ከመሰረዝ ባለፈ የሚወሰድ ዕርምጃ ስለመኖሩ አልተናገሩ

Aleta Land Group aims at opening a trans-border coffee shop in Asia

Image
It has finalized a partnership with Japanese firm to import green tea Aleta Land Coffee, a local coffee firm announced that it would a open trans-border coffee shop in Asia starting next year. It was made public last Saturday in Hawassa, regional capital of the Southern Nation Nationalities Peoples Regional State (SNNPR). Celebrating the 10th anniversary and inauguration of three factories in the town, Habetamu Silla, general manager of Aleta Land Group told The Reporter that establishing a trans-border coffee shop in Asia and worldwide is being undertaken along with importing green tea seedlings from Japan to send back in the form of soft drinks. Aleta Land Group was initially established in 2004 with a paid up capital of one million birr, which through years has grown to 62 million Br. “These days, many young Asians have started drinking coffee in addition to their well-known tea tradition,” Habtamu tells why his company is keen on opening coffee shops beside exporting

GETAWAYS FROM THIS INFERNAL CITY

The quiet roads, the beautiful scenery, the spectacular lake, comfortable rooms are definitely a gateway from Addis Ababa. ምንጭ፦ www.thereporterethiopia.com These days, the dusty roads of Addis, the cars honking, the concrete jungle, are becoming too much for people to handle. Due to that people like Natan Ayele can't wait for Friday in order to get out of the city. “Thank God it is Friday,” he says. Usually, his destination is Hawassa, which is located some 270 km south of Addis. Going to the Haile Resort relaxes him and traveling gives him freedom. Whether it is going to a quiet restaurant or staying at home, Addis is the last place he wants to spend his weekends. Haile Resort is a place where he sits for hours reflecting and reading. He sometimes takes a friend to enjoy the weekend with.  Usually, when people go out of the city they tend to drink more. However, he opposes the idea of intoxication. Rather, he just sits by the pool and might have a couple of glasses of

ፕሪሚየር ሊጉ ዛሬ በተለያዩ ጨዋታዎች ይቀጥላል

Image
ምንጭ፦ www.fanabc.com አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23 ፣ 2006 ( ኤፍ.ቢ.ሲ. ) 22ተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በሚደረጉ የተለየዩ ጨዋታዎች ይቀጥላል። መከላከያ ከሀዋሳ ከነማ 9 ሰዓት ላይ ሲጫወቱ ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከደደቢት 11 ሰዓት ከ30 ላይ በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይገናኛሉ። በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ደግሞ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ መድህን 10 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። በክልል ከተሞች ዳሸን ቢራ ከወላይታ ዲቻ ፣ ሙገር ሲሚንቶ ከመብራት ሃይል ፣ ሀረር ቢራ ከኢትዮጵያ ቡና ፣ አርባ ምንጭ ከነማ ከሲዳማ ቡና በተመሳሳይ 9 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ።

ሀዋሳ ቤሌማ……!

Image
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኣርት “መጓዝ ማወቅ ነው…..!” ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1995 ዓም (ከአስር ዓመት በፊት መሆኑ ነው) በወርሃ መስከረም ላይ በአሁን ሰዓት ላይ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል በዋና ከተማነት የምታገለግለውን ሃዋሳ ከተማ ለመጀመርያ ጊዜ ለማየት በቃሁ…..፡፡ በሃይቁ ላይ በነጻነት የሚደንሱ የተለያዩ አሶች፤ደስ በሚለው የማያቃጥለው ሞቃት አየሯ እና ሰማይ ላይ በደስታ የሚንሳፈፉ የተለያዩ አእዋፋት……! ባላቸው አቅም ሁሉ በፍቅር አና በደስታ እንግዶቿን የሚያስተናግዱ ህዝቦቿ ልብ የሚመስጥ ነበር…..፡፡ በዚያን ጊዜ ከተማዋ አቅም እንደሌለው…. ወላጅ  እንደረሳው…. የህጻን ልጅ ቁምጣ እዚም እዛም የተቦጨቀ የአስፋልትና የጠጠር መንገዶች፤በአሁን ሰዓት መሃል ፒያሳ ጎዳናን በኩራት ተኮፍሶ የሚታየውን የገብርኤል ቤተክርስቲያን ጨምሮ በጅምር የቀሩ ጥቂት ህንጻዎች፤የሃዋሳ ሃይቀርን ተከትለው እንደሚታዩት ግዙፍ የሾላ ዋርካ ዛፎች….እድሜ የጠገቡ አብዛኛውን አሮጌ ቤቶችና የቆዩ ትንንሽ ሆቴሎች…..ወዘተ…. የነበራት ሃዋሳ…. ውበትዋ ማርኮኝ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ እየተመላለስኩ ደስታዬን አጣጥሜያለሁ……!፡፡ እነሆ ዛሬ ከሁለት አመት ቆይ በኋላ ዳግም ተመልሼ እዛው እገኛለሁ ፡፡ እጅግ በሚገርም ሁኔታ ከተማዋ ተለውጣለች… አምራለች…!፡፡ በየጊዜው ለውጥ አለ የተጀመሩ ህንጻዎች አልቀው ሌሎች ተጀምረዋል፡፡በ1960ዎቹ አካባቢ 6ኪሎ ሜትር ብቻ ይሸፍን የነበረው የአስፋከልት መንገድ ዛሬ 56.6 ኪሎ ሜትር ደርሷል፡፡ ትንሽ የነበረው ወስጥ ለውስጥ የተቦዳደሰ መንገዶችዋ ዛሬ በኮብል ድንጋይ 18 ኪሎሜትር ያህል ተነጥፏል፡፡ ከሌሎች መሰል የሃገራችን ከተሞች በአንጻራዊነት ሲታይ በእድሜ ትንሽ ብትሆንም ተፈጥሮም እያገዛት እጅግ በፍጥነ

የኢህአዴግ 1 ለ 5 አደረጃጀት፣ ቀጣዩ ምርጫ እና የተቃዋሚዎች ስጋት

“በልማት ሰበብ አፈና የሚፈፀምበት መዋቅር ነው” - መኢአድ “1ለ5 አደረጃጀት ለምርጫው ስጋት አይሆንም”  - አንድነት “ፓርቲያችን፤ ህዝቡ የመዋቅሩ ሰለባ እንዳይሆን የማጋለጥ ሥራ ያከናውናል”  - መድረክ “ተቃዋሚዎችም እንደ ኢህአዴግ የፈለጉትን አደረጃጀት መፍጠር ይችላሉ”  - መኢአብ “ኢህአዴግ አፋኝ ሚሊሻ አድርጎ ያዘጋጃቸው ናቸው” - ኢዴፓ “አደረጃጀቱን ለምርጫ ይጠቀማል የተባለው የሃሰት ውንጀላ ነው”  - ኢህአዴግ ምንጭ፦ www.addisadmassnews.com መንግስት 1 ለ 5 የተሰኘውን አደረጃጀት ለፈጣን ልማታዊ እድገት እየተጠቀመበት እንደሆነ ይናገራል፡፡ በገጠር ይሄንኑ አደረጃጀት ለጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ተጠቅሞበት ባስገኘው ውጤት፣ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ አገራት ምሳሌ ለመሆን መብቃቱንም በኩራት ይጠቅሳል፡፡ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው፤ አደረጃጀቱ ፖለቲካዊ ግብን ያነገበ የስለላ መዋቅር ነው፣ የገዥው ፓርቲ የምርጫ ማስፈፀሚያና መቆጣጠሪያ መዋቅር ነው ሲሉ ይተቻሉ፡፡  ኢህአዴግ በ1 ለ 5  አደረጃጀት በመላው ሃገሪቱ የልማት እንቅስቃሴዎችን በማፋጠን ረገድ ስኬታማ እየሆንኩ ነው ቢልም ተቃዋሚዎች ግን ለአፈና እየተጠቀመበት ነው ይላሉ፡፡ “ከክልል ክልል፣ ከወረዳ ወረዳ ተዘዋውረን ህዝብን በአላማችን ስር ማሰለፍና ማደራጀት ቸግሮናል፣ አባላቶቻችንና ደጋፊዎቻችን እስራትና ድብደባን ጨምሮ ለብዙ እንግልት እየተዳረጉ ነው፣ እንኳንስ ሰፊ ህዝባዊ መሰረት ያለው አደረጃጀት ልንፈጥር በአንድ ወረዳ ውስጥ እንኳን  ፅ/ቤት መክፈት አቅቶናል፣ ከአዲስ አበባ ህዝብ የማደራጀት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የተሸኙ አመራሮች፣ የወረዳ ሹማምንት ሰለባ ይሆናሉ” የሚሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ ገበሬው 1 ለ 5 ካልተጠረነፈ፣ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር የመሳሰሉ የግብርና ግብአቶችን ማግኘት

Fair trade not helping workers who pick crops, study shows

Image
Fair trade monitoring process questioned in wake of findings in Ethiopia and Uganda A new study of plantations in Ethiopia and Uganda found casual workers who pick the coffee may be paid less on Fair Trade-dominated farms than on larger plantations or areas without a Fair Trade designation. (Kent Gilbert/Associated Press) The Fair Trade certification movement asks consumers of coffee, tea, sugar and chocolate to pay a little more for the product to help the people who grow and pick the coffee to a better life. But a new report by an economist from the University of London finds the Fair Trade certification movement may not be living up to its billing. THE CURRENT: How fair is fair trade?   Fair trade products hold their own during recession Christopher Cramer co-author of  Fairtrade, Employment and Poverty Reduction in Ethiopia and Uganda  studied 12 sites in Ethiopia in Uganda, comparing the wages of hired labour in areas with large plantations, areas with small f

መድረክ ሕይወታቸው ላለፈና ንብረታቸው ለወደመባቸው ዜጎች መንግሥት ካሳ እንዲከፍል ጠየቀ

Image
ምንጭ፦ www.ethiopianreporter.com   የአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞችን ተጠቃሚ የሚያደርገውን  የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን መሠራትን አስመልክቶ፣ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ባደረጉት ሰላማዊ ሠልፍ ላይ በተፈጠረ ግጭት ሕይወታቸው ላለፈ ቤተሰቦችና ንብረታቸው ለወደመባቸው ባለሀብቶች፣ መንግሥት ካሳ መክፈል እንዳለበት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ጠየቀ፡፡  መድረክ ‹‹ለሰላማዊ ተቃውሞ ጥይት ምላሽ ሊሆን አይገባም›› በሚል መሪ ቃል ግንቦት 16 ቀን 2006 ዓ.ም. መነሻውን ከግንፍሌ ወንዝ ድልድይ አድርጐ በቤልኤር ሆቴል፣ በህንድ ኤምባሲ፣ በአዋሬ አደባባይና በአድዋ ድልድይ በማድረግ በድንበሯ እናቶችና ሕፃናት ሆስፒታል ጀርባ በሚገኘው የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ሜዳ ላይ ባጠናቀቀው ሰላማዊ ሠልፍ ላይ፣ ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ሐሳቦችን አቅርቧል፡፡ የመድረክ አባልና የፓርላማ ተመራጭ የነበሩት አቶ ገብሩ ገብረ ማርያም መድረክ ለምን ሰላማዊ ሠልፍ ለማድረግ እንደተገደደ ሲናገሩ፣ ‹‹ኢሕአዴግ ራሱ ላወጣው ሕገ መንግሥት ባለመገዛት ኢሕገ መንግሥታዊነቱን አረጋግጧል፡፡ ትግላችን ኢዲሞክራሲያዊ ሒደቶች እንዲታረሙ ነው፡፡ በአገሪቱ በተለይ በኦሮሚያ ክልል የተከሰተው ችግር የዲሞክራሲና የሕገ መንግሥታዊ አስተዳደር እጦት ነው፤›› ብለዋል፡፡  ሕገ መንግሥቱ ሲጣስ ‹‹መብቴ ተጥሷል›› ማለት ሕገ መንግሥታዊ መብት መሆኑን የገለጹት አቶ ገብሩ፣ የአዲስ አበባንና የልዩ ዞኖቹን የጋራ ልማት ትስስር ሽፋን፣ ሕዝብ ያልተወያየበትንና ያልተስማማበትን ለመተግበር መነሳት ኢሕገ መንግሥታዊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሕዝቡና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያነሱ

ማንን እንስማ፦ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ገለጹ፤ የዓለም ምግብ ድርጅት ፋኦ በበኩሉ በኣገሪቷ ከ2 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል ይላል

Image
የዜናው ምንጭ፦  www.ena.gov.et አዲስ አበባ ግንቦት 20/2006 ኢትዮጵያ በሁለት አሥርት ዓመታት ውስጥ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በአገር አቀፍ ደረጃ በምግብ ራሷን መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በአዲስ አበባ ስታዲዬም በተከበረው 23ኛው የግንቦት 20 የድል በዓል የማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት ባለፉት 20 ዓመታት በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡ ፕሮግራሞች ተግባራዊ በመሆናቸው ስኬታማ ውጤት ተመዝግቧል። ከሦስት ዓመታት በፊት የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ አገሮች ባለፉት ስድስት አሥርታት ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በድርቅ ክፉኛ ተመተው እንደነበር አስታውሰው፣ ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት ያለአንዳች መሰናክል ችግሩን ማለፏን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከ23 ዓመታት አገሪቱ ከነበረችበት ከፍተኛ ተመጽዋችነት በመውጣት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በዓመት ከ250 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ማምረቷንም አቶ ኃይለማርያም ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት አርሶ አደሩ ከፍተኛ ገቢ ወደሚያስገኙ ምርቶች መሸጋገሩንና በቀጣይም ጠንካራ አገር በቀል ባለሃብቶችን በማፍራት የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ ጥረት ይደረጋል። ለሁለት አስርት ዓመታት በተካሄደው እልህ አስጨራሽ ትግልም አገሪቱ በዓለም ኅብረተሰብ ዘንድ ትታወቅበት ከነበረው ረሃብና ጉስቁልና በመውጣት ከኦክስፎርድ የእንግሊዝኛ መዝገበ-ቃላትም የረሃብተኝነት ምሳሌ መሆኗ እንዲፋቅ መደረጉን ተናግረዋል።ይህም ለኢትዮጵያውያን ታላቅ እመርታ መሆኑን ጠቅሰዋል።  በቀጣይም ኢትዮጵያ ከሚፈለገው ምርታማነትና የብልፅግና ደረጃ ለመድረስና ግሎባላይዜሽን የደቀነውን የውድድር ፈተና በብቃት ለማለፍ  ዜጎች ከመንግስት