POWr Social Media Icons

Thursday, January 9, 2014

የሲዳማ መዲና የሆነችው ሃዋሳ ከተማ ላለፉት 19 ኣመታት የከተማዋ ባለበት በሆኑት የሲዳማ ተወላጆች መተዳደር ከጀመረች ወዲህ በመጤዎች ለግማሽ ምዕተኣመት ሲትተዳደር ካሳየችው እድገት በላይ በማስመዝገብ በኣሁኑ ጊዜ በኣገሪቱ ከምገኙ ግንባር ቀደም የክልል ከተሞች ኣንዷ ልትሆን በቅታለች። ብሎም ከተማዋ ኣገሪቱ በማስመዛገብ ላይ ላለችው የኢኮኖሚ እድገት ተጨባጭ ማሳያ ሆናለች።

ሃዋሳ በተለይ ባለፉት 10 ኣመታት ለነዋሪዎቿ ምቹ እንዲትሆን በማለም ትምህርት እና ጤናን ጨምሮ በሌሎች መሰረታዊ ኣገልግሎት ዘርፎች፤ በመንገድ፤በኃይል እና ውሃን ጨምሮ በሌሎች ኢንፍራስትራክቼርን በማስፋፋት ረገድ ውጤታማ ስራዎች ከተሰሩባቸው የኣገሪቷ ከተሞች ኣንዷ ናት። በመልካም ኣስተዳደር ላይ የምታዩትን ኣንዳንድ ችግሮችን በመቅረፍ ስራዎች በከተማዋ ኣስተዳደር በመስራት ላይ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ውስጥ መልካም ውጤት ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

እንግዲህ የሃዋሳ ከተማ በየኣመቱ በምካሄደው የኢትዮጵያ ከተሞች ሳምንት ውድድር ላይ ለነዋሪዎቿ ኑሮ ምቹነት በተለያዩ ዘርፎች ባካሄደቻቸው መልካም ስራዎች በምርጥ ከተማነት በመመረጥ በተደጋጋም ኣሸናፊ መሆኗ ከተማዋን የሚያስተዳድሩት ሲዳማውያ ኣይደለም ከተማ እና ዞንን ቀርቶ ክልልን በብቃት ማስተዳደር እንደምችሉ ያስመሰከሩበት ነው።

የሃዋሳ ከተማ የኢንዱስትሪ እና የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የከተማዋ ኣስተዳደር ለያዘው እቅድ መሳካት ኣስተዋጽኦ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል የኣውሮፕላን ማረፊያ መኖር ወሳኝ ቢሆንም ከተማዋ ያለ ኣውሮፕላን ማረፊ ቆይታለች። ለሃዋሳ ከተማ በኣየር ማረፊያነት የሚያገለግለው ከሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ ፊትለፊት ያለ ሜዳ ሲሆን፤ ይህ ሜዳም ሂልኮፕቴር እና ትናንሽ ኣውሮፕላኖች ለማሳረፊያነት ያለፈ ኣገልግሎች ኣይሰጥም። የዛሬ ሁለት ኣመት የኃይሌ ሪዞርት መመረቅን ተከትሎ ባለሃብቱ ኣትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ ከከተማዋ ኣስተዳደር ጋር በመተባበር ኣየር ማረፊያውን ለማስፋት እንደምፈልግ የተናገረ ብሆንም በተግባር የተሰራ ስራ ግን ኣልነበረም። ሆኖም ሰሞኑን ከኣገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እንደተሰማው ከሆነ የሃዋሳ ከተማ ዘመናዊ ኣየር ማረፊያ ልገነባላት ነው።  
እንደሬዲዮ ፋና ዘገባ ከሆነ፦ የሃዋሳ ከተማ ኤርፖርት ግንባታን ለመጀመር የሚያስችለው የቦታ ርክክብ ተካሂዶ የዲዛይን ስራ ተጀመሯል አለ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ።የደቡብ ብሄሮችና ብሄረሰቦች ክልል ርዕሰ መዲና ሀዋሳ ፥ በ2005 ዓ.ም ከ631 ሺህ በላይ በሆኑ የውጭና የሀገር ውስጥ ዜጎች ተጎብኝታ 130 ሚልዮን ብር አስገኝታለች። 

የክልሉ ባሀልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘሪሁን ዘውዴ ፤ ከተማዋ የአይን ማረፊያ ሳታጣ ወደ እልፍኟ የሚያደርስ አማራጭ የትራንስፖርት መንገድ በማጣት ብቻ ያሰበችውን ያህል ጎብኝ እንዳላገኘች ተናግረዋል። ብቸኛው የመጓጓዠ ዘዴ ተሽከርካሪ ብቻ መሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች አቅማቸው የቻለውን ፣ ቀልባቸው የወደደውን የመጓጓዥ ዘዴ እንዳይጠቀሙም ምክንያት ሆኗል።

ለዚህም የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት  ቦታ ተረክቦ የኤርፖርቱን ዲዛይን በማሰራት ላይ ነው።ለዲዛይኑ አንድ ሚሊየን ብር የተመደበ ሲሆን፥  በአራት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል።ለግንባታው የሚወጣው ወጪና የግንባታው ጊዜም ከዲዛይኑና ጨረታው መጠናቀቅ በኋላ የሚታወቅ ይሆናል ይላሉ የድርጅቱ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ወንድም ተክሉ።ይህ በሂደት ላይ ያለውና ሀዋሳ አሻግራ የምታማትረው ኤርፖርት ሲጠናቀቅ ፤ መዲናይቱ አጥብቃ የምትሻውን የቱሪስት ፍሰቷን በእጥፍ የማሳደግ ግብ ጥርጊያው ይሰናዳለታል።

ወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ከውስጥ ኣዋቂ ምንጮች ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ፦ ኣዲሱን ኣውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት ሁለት ቦታዎች ተመርጠው እየተጠኑ ያለ ሲሆን ፤  እነዚህ የተመረጡት ቦታዎች ኣንደኛው በሸቤዲኖ ወረዳ ውስጥ ሌላኛው ደግሞ ዶሬባፋኖ ወረዳ ውስጥ ሁለቱም ሲዳማ ዞን ማለትም በቀድሞው የሃዋሳ ዙሪያ ወረዳ ውስጥ ይገኛሉ።
   
የኣውሮፕላን ማረፊያ መገንባቱ ለከተማዋ ሁለገብ እድገት ያለው ኣስተዋጽኦ ከፍተኛ ከመሆኑ ባሻገር በሲዳማውያን የምመራው የከተማዋ ኣስተዳደር ሃዋሳን በምስራቅ ኣፍሪካ ለኑሮ የተመቸች እና የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የያዘውን እቅድ ለማሳካት ያስችለዋል።