የሲዳማን ራስገዝ ክልላዊ መንግስት ለመመስረት በህዝብ ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ የነፈገው የኢትዮጵያ መንግስት በጎሮቤት ኣገር ሶማሊያ ክልላዊ መንግስታት እንድመሰረቱ በመስራት ላይ መሆኑ ተሰማ

የሲዳማን ራስገዝ ክልላዊ መንግስት ለመመስረት በህዝብ ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ የነፈገው መንግስት በሶማሊያ ክልላዊ መንግስታት እንድመሰረቱ በመስራት ላይ መሆኑ ተሰማ።

ወሬው የኣገሪቱ ዜና ኣውታሮች ነው፦

ፎቶ፦ ኢብኮ

በኢትዮጵያ ነጻ የወጡ የሶማሊያ አካባቢዎች የክልል መስተዳድር መሰረቱ

በአሚሶም ጥላ ስር የዘመተው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከአልሻባብ ነጻ ያወጣቸው የቦኮላ በይና ታችኛው ሸበሌ ግዛቶች በጋራ የደቡብ ምእራብ ሶማሊያ ክልላዊ አስተዳደር መሰረቱ::
በሶማሊያ የሚገኘው የቀጠናውና የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ገብረመድህን ፈቃዱ እንዳሉት የሶስቱን ግዛቶች ፖለቲከኞች አቀራርቦ በማወያየትና በክልላዊ የመንግስት ምስረታው የኢትዮጵያ ሰራዊት ከፍተኛ ሚና ነበረው::
የፌዴራል ስርአት እየገነባች ባለችው ሶማሊያ ሶስቱ ግዛቶች ክልላዊ አስተዳደር መመስረታቸው እየተዳከመ የመጣውን የአልሻባብን ሀይል ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል::
ምንጭ፦ ኢብኮ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር