ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ አለም አቀፍ የቦንድ ሸያጭ ገበያን ዛሬ ትቀላቀላለች

(ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ዛሬ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ አለም አቀፍ የቦንድ ሸያጭ ገበያን ትቀላቀላለች ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
ለሽያጭ ይቀርባል ተብሎ የሚጠበቀው የቦንድ መጠንም 1 ቢሊየን ዶላር መሆኑ ተነግሯል።
አገሪቱ ከቦንድ ሽያጩ አስቀድሞ በአገሪቱ ውስጥ ስላሉ ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎችና በምትሸጠው ቦንድ የምታገኘውን ገንዘብም ለምን ለምን ተግባራት ልታውለው እንዳሰበች በአውሮፓና በአሜሪካ ለሚገኙ የገንዘብ አበዳሪ ባለሀብቶች ለአንድ ሳምንት የዘለቀ ገለፃ ስታደርግ ቆይታለች።
ይህን ገለፃዋንም ትናንት ለመጨረሻ ጊዜ በአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ ለሚገኙ ባለሀብቶች በማቅረብ ማጠናቀቋንም ፋይናንሽያል ታይምስ ዘግቧል።
በኒውዮርክ ገለፃ ላይ የተገኙት ባለሀብቶችም በአጠቃላይ ኢትዮጵያ እየተጓዘችባቸው ስላሉት ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ተብራርቶላቸዋል።
እንደዘገባው ከሆነ በዛሬው ዕለት ጄ ፒ ሞርጋንና ደች ባንክ የኢትዮጵያን ቦንድ ለአለም አቀፍ አበዳሪ ባለሀብቶች ይዘው እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ የተበደረችውን ገንዘብም በ10 ዓመታት ውስጥ የምትመልስ ይሆናል።
የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ በዚህ ዓመት ኢኮኖሚያቸው በፍጥነት ይመነደጋል ብል ካስቀመጣቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያን በስምንተኛነት አስቀምጧታል።
የኢትዮጵያ መንግስት ኢኮኖሚያዊ ዕድገቱን ለማስቀጠል ያለው ቁርጠኝነትም ቦንዱን ለሚገዙ የገንዘብ አበዳሪ ባለሀብቶች አስተማማኝ እፎይታን እንደሚያጎናፅፋቸው ተገምቷል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር