ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ከደደቢት ተረከበ

ትናንትና በተደረጉ 4 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች አዳማ ከነማ እና ሲዳማ ቡና ድል አድርገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ በአስገራሚ መልኩ አቻ ተለያይቷል፡፡
በአዲስ አበባ ስታድየም 9፡00 ላይ መከላከያ አርባምንጭ ከነማን አስተናግዶ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡ ጨዋታው ተመጣጣኝ የነበረ ሲሆን አልፎ አልፎ ከተደረጉ ሙከራዎች ውጪ ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ሳይታይበት ተጠናቋል፡፡
ቀጥሎ በአዲስ አበባ ስታድየም የተካሄደው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሙገር ሲሚንቶ ጨዋታ በግቦች እና ሙከራዎች እንዲሁም በፈጣን እንቅስቃሴዎች የታጀበ ጨዋታ ነበር፡፡ ንግድ ባንኮች በመጀመርያዎቹ 5 ደቂቃዎች 3 ያለቀላቸው የግብ እድሎችን ያመከኑ ሲሆን ፊሊፕ ዳውዚ በ17ኛው ደቂቃ በፊሊፕ ዳውዚ ፣ በ37 ኛው ደቂቃ በአዲሱ ካሳ በተቆጠሩ ግቦች 2-0 መርተው የመጀመርየውን አጋማሽ አጠናቀዋል፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ ሙገር ሲሚንቶዎች ግርማ ኃ/ዮሃንስ በወሰዱት የተጫዋች ቅያሪ እርምጃ ታግዘው ባልተጠበቀ ሁኔታ አከታትለው ባስቆጠሯቸው ግቦች ወሳኝ አንድ ነጥብ ይዘው ተመልሰዋል፡፡ ለሙገር ሁለቱንም ግቦች ከመረብ ያሳረፈው ተቀይሮ የገባው ጋናዊው አጥቂ ጌድዮን አካፖ ነው፡፡
አዳማ ላይ ዘንድሮ ፕሪሚየር ሊጉን የተቀላቀሉት አዳማ ከነማ እና ወልድያ ተገናኝተው አዳማ ከነማ በቀላሉ 3-1 አሸንፎ የውድድር ዘመኑን የመጀመርያ 3 ነጥብ አሳክቷል፡፡
ይርጋለም ላይ በሜዳው ጠንካራ የሆነው ሲዳማ ቡና 1-0 ከመመራት ተነስተው በመጨረሻዎቹ 15 ደቂቃዎች ባስቆጠሩት ግብ ዳሽን ቢራን 2-1 አሸንፈው የሊጉ መሪነትን ከደደቢት የተረከቡበትን ድል አስመዝግበዋል፡፡
ቀሪዎቹ 3 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በብሄራዊ ቡድኑ ዝግጅት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘሙ ሲሆን ፕሪሚየር ሊጉን ሲዳማ ቡና በ7 ነጥብ የደደቢቱ ሳሚ ሳኑሚ በ4 ግቦች ይመራሉ፡፡
ምንጭ፦ http://www.soccerethiopia.net/en/premier-league/458-2014-11-09-17-08-28

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር