ኣስልጣኝ ማሪያኖ በሃዋሳ ከነማ የፊት መስመር ተጨዋች ላይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋች ለተፈጸመው ጥፋት ቀይ ካርድ ይገባው ነበር በማለት ለተጎጂው የሃዋሳ ከነማ ድምጻቸውን በማስማታቸው በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ልከሰሱ መሆኑ ተሰማ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኣስልጣኝ ማሪያኖ የሐዋሳ ከነማና የቅዱስ ጊዮርጊስን በኣዲስ ኣበባ ስታዲዮም ባደረጉት የሁለተኛ ሳምንት ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ የቅዱስ ጊዮርጊሰ ተከላካይ ኡጋንዳዊው አይዛክ ኤሴንዴ በሐዋሳ ከነማው የፊት መስመር ተጨዋች ታፈሰ ተስፋዬ ላይ ለፈጸመው ጥፋት ቀይ ካርድ ይገባው ነበር በማለት ለተጎጂው የሃዋሳ ከነማ ድምጻቸውን በማስማታቸው በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ልከሰሱ መሆኑ ተሰምቷል።


ዝርዝር ወሬው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው፦  

የተከታተሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ‹‹በዳኛ ውሳኔ ጣልቃ ገብተዋል›› በሚል በቅዱስ ጊዮርጊስ ክስ ሊመሠረትባቸው መሆኑ ተሰማ፡፡
ለቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ቅርበት ያላቸው የሪፖርተር ምንጮች እንደሚናገሩት ከሆነ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ሐዋሳ ከነማ የሁለተኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታቸውን በአዲስ አበባ ስታዲዮም ባከናወነበት ዕለት፣ የቅዱስ ጊዮርጊሰ ተከላካይ ኡጋንዳዊው አይዛክ ኤሴንዴ በሐዋሳ ከነማው የፊት መስመር ተጨዋች ታፈሰ ተስፋዬ ላይ ጥፋት ይፈጽማል፡፡ 
የዕለቱ ጨዋታ የመሐል ዳኛ ለአይዛክ ቢጫ ካርድ ከሰጡ በኋላ ቅጣት ሞት ለሐዋሳ ከነማ ሰጥተው ጨዋታው እንዲቀጠል ያደርጋሉ፡፡ የዳኛውን ውሳኔ ተከትሎ አሠልጣኝ ማሪያኖ ‹‹በፍፁም ይኼ ጥፋት የሚገባው ቢጫ ካርድ ሳይሆን ቀይ ካርድ›› በማለት ተቃውሞዋቸውን ያሰማሉ፡፡ ክለቡም በጉዳዩ ሲመክርበት መቆየቱንም ምንጮቹ ይገልጻሉ፡፡
ክለቡ በመጨረሻም አሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ የብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኝ እንደመሆናቸው ከክለቦች የውስጥ ጉዳይ ገለልተኛ መሆን እንደነበረባቸው ያም አልበቃ ብሏቸው ውሳኔውን ከመቃወማቸው አልፎ ተርፎ የዕለቱን የጨዋታ ታዛቢ ዳኛን ሙግት የገጠሙበት መንገድ አግባብ አለመሆኑን በመግለጽ ክስ ሊመሠረትባቸው መወሰኑ ነው የተሰማው፡፡ 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር