በቀርከሃ ተክል ላይ ያተኮረ አለማቀፍ ጉባኤ በቀጣዩ ሳምንት በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በግብርና ሚኒስቴር የዘላቂ መሬት አያያዝ  ፕሮግራም አማካሪ አቶ መላኩ ታደሰ  እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ ለቀርከሀ ምርት ያላት ምቹነት ጉባኤውን እንድታስተናግድ አስመርጧታል።

በጉባኤው የግሉ ዘርፍ ለቀርከሃ ልማት በሚኖረው ድርሻ እንዲሁም ቀርከሃ ለተፋሰስ ልማት በሚኖረው ሚና  ዙሪያ ጥናቶች ቀርበው ውይይት ይደረጋል።
ቀርከሀ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ለኢኮኖሚ እድገትና የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ  ለመለወጥ የሚኖረው አስተዋጽኦም የጎላ መሆኑን ነው አቶ መላኩ የተናገሩት።
ኢትዮጵያ 1 ሚሊዮን ሄክታር ላይ ያረፈ የቀርከሃ ምርት ያላት ሲሆን፥ ከአፍሪካ በአጠቃላይ ካለው ምርት 67 በመቶውን ትሸፍናለች፡፡
ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ.

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር