ኢትዮጵያ ከቡና ምርቷ የተሻለ ተጠቃሚ እንድትሆን እየሰራ ነው- ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 1፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ከቡና ምርቷ የተሻለ ተጠቃሚ እንዳትሆን የሚያደርጉ ማነቆዎችን ለማስወገድ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት  እየተሰራ መሆኑን ግብርና ሚኒሰቴር አስታወቀ።
በሚኒስቴሩ የቡና ሻይና ቅመማ ቀመም ዳይሬክተር አቶ ፍቅሩ አመኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት በህገ ወጥ መንገድ ከሃገር ሾልኮ የሚወጣ፣ ከአካባቢ  አካበቢ የሚፈጠረው የዝርያ መቀላቀልና ህገ ወጦች ህጋዊ ነጋዴዎችን ከገበያ እንዲወጡ ማድረግ ከማነቆዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው።
ዳይሬክተሩ እነዚህ ችግሮች በተለይም ቡና አብቃይ በሆኑ ምስራቅ ወለጋ፣  ሃረርጌና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ አካባቢዎች ሚኒስቴሩ ባደረገው ምልከታ መስተዋላቸውን ተናግረዋል።
የመን ከሃረርጌ ሾልኮ የሚወጣውን  ሞካ የተባለ ቡና የራሴ ነው ብላ በሳውዲአረቢያ ለገበያ ማቅረቧ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሚወጣው ቡና ደግሞ ደቡብ ሱዳን ገበያ ላይ ይውላል የሚል ግምገማ መኖሩን ገልጸዋል።
ይህንን ችግር ለማስወገድ የግብርናና ንግድ ሚኒስቴሮችን ጨምሮ ከቀበሌ እስከ ፌደራል በበጀት የተዋቀረ ግብረ ሃይል መዋቀሩን ጠቅሰዋል።
በመጪው ህዳር ወር በደቡብ ክልል አዘጋጅነት በሚከበረው በቡና ቀንና በተለያዩ አጋጣሚዎች ህብረተሰቡ እንዲህ አይነት ህገ ወጥነትን በጋራ እንዲከላከል ሰፊ ግንዛቤ የማስጨበጡ ስራ ይከናወናል ብለዋል።
ዘንድሮ  በቡና ከለማው  850 ሺ ሄክታር መሬት ከ6 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።
ባለፈው አመት 5 ሚሊየን ኩንታል የሚጠጋ የቡና ምርት መገኘቱን ዳይሬክተሩ አቶ ፍቅሩ አመኑ ተናግረዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር