ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል የማጅራት ገትር በሽታ መከላከያ ክትባት እየተሰጠ ነው

Photo: Wikipedia 

በደቡብ ክልል የማጅራት ገትር በሽታ መከላከያ ክትባት እየተሰጠ ነው

ሀዋሳ ጥቅምት 8/2007 በደቡብ ክልል ከ11 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ተደራሽ የሚያደርግ የማጅራት ገትር በሽታ መከላከያ ክትባት የመስጠት ዘመቻ ዛሬ መጀመሩን የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ገለጸ፡፡
በቢሮው ጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ጀማል ሀሰን እንደገለጹት ክትባቱ በዘመቻ የሚሰጠው ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ለአስር ቀናት ነው፡፡
በዚህ በክልሉ 11 ዞኖችና አራት ልዩ ወረዳዎች ዕድሜያቸው ከ1 እስከ 29 ዓመት የሆናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባቱ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡
አቶ ጀማል እንዳስረዱት  ሞቃታማ ፣ደረቅና ነፋሻማ የሆነውን የአየር ንብረት ተከትሎ በወረርሽኝ መልክ ሊከሰት የሚችለውን የማጅራት ገትር በሽታ አስቀድሞ ለመከላከል ክትባቱ ይሰጣል ፡፡
ከሁለት አመት በፊት በክልሉ ቤንች ማጂ ፣ ሸካ ደቡብ ኦሞና ካፋ ዞኖች የመጀመሪያ ዙር የመከላከያ ክትባት መሰጠቱን አመልክተዋል፡፡
ሁለተኛው ዙር የማጅራት ገትር በሽታ መከላከያ ክትባት ደግሞ በቀሪዎቹ የክልሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በዘመቻ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡
ዘመቻውን ለማሳካትም  በክትባቱ ለሚሳተፉ በየደረጃው ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱም ተመልከቷል፡፡
ክትባቱ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች በጤና ተቋማትና ህዝብ በብዛት በሚገኝባቸው አካባቢዎች ማዕከላት እንደሚሰጥና ለክትባቱ አስፈላጊ የሆኑ መድሀኒቶችና ሌሎች ተጓዳኝ ቁሳቁሶች መሰራጨታቸውም  የስራ ሂደት ባለቤት ገልጸዋል፡፡
ህብረተሰቡም ይህንን አውቁ በየአካባቢው ባሉ የክትባት ማዕከላት በመገኘት ልጆቹን ማስከተብ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
በዚህ ዘመቻም በክልሉ የሚኖሩ 11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሰዎች ይከተባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜኣ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር