POWr Social Media Icons

Monday, October 20, 2014

 የፋሽን ኢንዱስትሪ እየተስፋፋ ከመጣበት ዘመን አንስቶ በርካታ የአለባበስ ልምዶችም አብረው ተፈጥረዋል። በተለይ በአውሮፓውያኑ አካባቢ አንድን ልብስ ከመምረጣቸው በፊት ለምን ጉዳይ እንደሚለብሱትና በምን ወቅት እንደሚያዘወትሩት ጠንቅቀው ማወቅ ይጠበቅባቸዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በአገራችን የሚዘጋጁ ባህላዊ አልባሳት ጊዜና ቦታ ተመርጦላቸው እንዲለብሱ እየሆነ ነው።
ብዙ ጊዜ የባህላዊ አልባሳት በበዓላት ቀን ላይ ብቻ እንዲለበሱ የተወሰኑ ነበሩ። አሁን አሁን ግን የባህላዊ አልባሳትን በዘመናዊ መንገድ በማዘጋጀት በተለያዩ ወቅቶች በማንኛውም ቦታ እንዲለበሱ እየደተረገ ነው።

በሐዋሳ ከተማ የሚገኘው አበባ ሹራብና ባህላዊ አልባሳት ማምረቻና ማከፋፈያም ከአገራችን አልፎ እስከ ውጭ አገር ድረስ ባህላዊውን አልባሳት በዘመናዊ መንገድ በማዘጋጀት ዕውቅናን እያተረፈ መጥቷል፡፡ 

0 comments :