POWr Social Media Icons

Thursday, October 23, 2014

የጡት ካንሰር ህክምና በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠት ሊጀመር ነው

የጡት ካንሰር ህክምናን በ5 ዩኒቨርሲቲዎች ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን በጡት ካንሰር ዙሪያ የሚሰሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ገለጹ።
ይህን ህክምና ለመጀመር የሚያስችል የመሳሪያና የባለሞያ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
ህክምናው የሚሰጠው በጅማ፣ ሃዋሳ፣ መቀሌ፣ ጎንደር እና ሃሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ነው።
ዓለም አቀፉ የጡት ካንሰር ቀን ጥቅምት 16 በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበርም አዲስ አበባን ጭምሮ በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ እና ትግራይ ክልሎች የእግር ጉዞ በማካሄድ ነው።
የዚህ በአል አላማ ህብረተሰቡ የጡት ካንሰርን አስቀድሞ የመከላከል፣ የምርመራና የህክምና አማራጮችን ግንዛቤ ማሳደግ ነው።
የጡት ካንሰር ህመምን ሙሉ ለሙሉ አስቀድሞ መከላከል ባይቻልም ህመሙ እንደተከሰት ተገቢው ህክምና ከተሰጠ የመዳን እድሉ  ሰፊ ነው።
የዕድሜ መግፋት፣ ከመጠን ያለፍ ክብደት፣ አልኮል መጠጣት፣ ጡት አለመጥባትና መሰል ምክንያቶች ለጡት ካንሰር እንደሚያጋልጥ የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ።
ምንጭ፦ EBC

0 comments :