መንግስት የገንዘብ ምጣኔ ማስተካከያ እንደማያደርግ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የገንዘብ ምጣኔ ማስተካከያ እንዲደረግ የሚያስገድድ የኢኮኖሚ ሁኔታ ባለመኖሩ መንግስት የማስተካከያ እርምጃ እንደማይወስድ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር አስታወቁ።
ሚኒስትሩ አቶ ሱፍያን አህመድ እንዳሉት፥ በአሁኑ ወቅት የብር ምጣኔ እንዲለወጥ የሚፍለጉ የኢኮኖሚ ምክንያቶች የሉም።
ይህ በሌለበት ሁኔታ መንግስት የገንዘብ ምጣኔ ማስተካከያ እንደማያደርግ ህብረተሰቡም ሆነ ባለሀብቱ ሊገነዘብ ይገባል ብለዋል።
ቀጣዩ የአምስት ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድም ማስተካከያ እንደማይደረግ ታሳቢ ተደርጎ መዘጋጀቱን ነው ያረጋገጡት።
በቅርቡ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ብር ከሚገባው በላይ ጥንካሬን እንደያዘ በማንሳት መንግስት የገንዘብ ምጣኔ ማስተካከያ በማድረግ ጥንካሬውን እንዲቀንስ መክሮ ነበር።
አቶ ሱፍያን መንግስት በእንደዚህ ዓይነቱ የየትኛውም ወገን ጫና እንደማይሰራ በመግለፅ ማስተካከያው አይደረግም በሚለው አቋሙ መፅናቱን ጠቁመዋል።
በአውሮፓውያኑ 2011 ላይ የገንዘብ ምጣኔ ማስተካከያ ተደርጎ በ20 በመቶ የብር ዋጋ ዝቅ መደረጉ ይታወሳል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር