ዛምቢያ የመጀመሪያውን ነጭ መሪ ጊዚያዊ ፕሬዝዳንት አድርጋ ሾመች

አዲስ አበባ ጥቅምት 20/2007 ዛምቢያ ፕሬዝዳንቷን በሞት ካጣች በኋላ የአገሪቱ ካቢኔ አዲስ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት መሾሟን ዘ ኒዮርክ ታይምስ ዘገበ።
የአገሪቱ ካቢኔ ትናንት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ  የአገሪቱ  ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩትን ጌይ ስኮትን በጊዜያዊነት ሰይሟል።
የእንግሊዙ ዜና ማሰራጫ ቢቢሲ የዛምቢያን መከላከያ ሚኒስትር ኢድጋር ሉንጉን እንደዘገበው ደግሞ የዘር ሃረጋቸው ከስኮትላንድ የሚመዘዙት ሚስተር ስኮት ዛምቢያ ከቅኝ አገዛዝ ነጻ ከወጣች በኋላ የአገሪቱ የመጀመሪያው ነጭ የአገር መሪ ያደርጋቸዋል።
ጌይ ስኮት የፕሬዝዳንትነት ምርጫው በ90 ቀን ውስጥ እስከሚካሄድ ድረስ በተጠባባቂነት አገሪታን ይመራሉ።
የ70 ዓመቱ አዛውንት ጌይ ስኮት ከዚህ ቀደም አርሶ አደር፣የግብርና ባለሙያና የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ሆነው መሰራታቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል።
በተጨማሪም ሚስተር ስኮት በተለያዩ ሃላፊነቶች፣ የሚኒስቴር ቦታዎችና እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር  ከ2011 እስከ 2014 በምክትል ፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል።
የሚስተር ስኮት እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1994 የደቡብ አፍሪካ መሪ የነበሩት ኤፍ ዴ ክለርክ ከስልጣን ከወረዱ በኃላ ከሳሃራ በታች የመጀመሪያው ነጭ መሪ ሆነው መመረጥ በአለም አቀፍ ብዙሃን መገናኛ ተቋማት አዎንታዊና አሉታዊና አስተያዬቶችን እየሰጡ ነው።
ዛምቢያን ለ3 አመታት የመሩት የ77 አመቱ ሚካኤል ሳታ ከትናት በስቲያ በሞት መለየታቸው ይታወሳል።
ምንጭ፦ ኢዜኣ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር