በኮንፈረንሱ የኢትዮጵያን ቡና ለማሰተዋወቅ ታስቧል

በሶስተኛው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ቡና ኮንፈረንስ የአገሪቱን ቡና በስፋት በማስተዋወቅና የጥራት ደረጃውን በሚያሳድጉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር አስታወቀ።
የማህበሩ የሥራ አመራር ቦርድ ፕሬዝዳንት አቶ ሁሴን አድራው እንደተናገሩት ማህበሩ በሚያዘጋጀው ተመሳሳይ ጉባኤ በአለም አቀፍ ደረጃ የትላልቅ ቡና ገዥ ኩባንያዎችንና ከቡናዘርፍ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ድርጅቶችን ትኩረት መሳብ ተችሏል።
ከጥቀምት 27 ጀምሮ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ቡና ኮንፈረንስም አገሪቱ በቡናው ዘርፍ ያላትን ሚና በማሳየትም ትልቅ የገጽታ ግንባታ መድረክ ይሆናልም ብለዋል።
በኮንፈረንሱም አገሪቱ ወደ ውጭ የምትልከው ቡና ጥራት ደረጃን በመገምገም ደረጃውን ይበልጥ ለማሻሻል በሚያስችሉ ነጥቦች ላይ ትኩረት ይደረጋል።
በኮንፈረንሱ ከቻይና፣ ከደቡብ ኮሪያ፣ ከህንድ እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ታዳሚዎች ይፈሉበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል። 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር