ዘንድሮ የቡና ምርትና ዋጋ ጭማሪን በመጠቀም የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ዝግጅት ተደርጓል-አቶ ከበደ ጫኔ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዘንደሮ አመት የሚኖረውን የቡና ምርትና ዋጋ ጭማሪ ተጠቅሞ የተቀመጠው ግብ ለማሳካት በቂ ቅድም ዝግጅት ተደርጓል አሉ የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከ98 ከፍተኛ ቡና ላኪ ድርጅቶች ጋር በ2007 የቡና የውጭ ንግድ እቅድ ላይ ውይይት አካሂዷል።
ሚንስትሩ ዘንድሮ 235 ሺህ ቶን ቡና ለመላክና ከ840 ሚለዮን ዶላር በላይ ለማግኘት መታቀዱን ተናግረዋል።
ዘንድሮ ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀው ከ435 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርትና በአለም አቀፍ የገበያ ቡና ዋጋ መጨመር እቅዱን ለማሳካት በአመቺ ሁኔታነት ተጠቅሰዋል።
ሆኖም ቡና ላኪዎች ህገ ወጥ የቡና ንግድና የትራንስፖርት ዋጋን በእክልነት አንስተዋል።
ሚኒስትሩ አቶ ከበደም ህገ ወጥ ንግዱን ለመከላከል ከ13 በላይ ኬላዎች መቋቋማችውንና የሎጅስቲክስ ችግርን ለመፍታት ፤ ለቡና አቅራቢና ላኪዎች ቅድሚያ እንዲሰጥ ለማድረግ መታቀዱን አንስተዋል።
እነዚህ ቅድመ ዘግጅቶች በአመቱ ለማግኘት የታቀደውን የገንዘብ መጠን ለማሳካት መሰረት ናቸውም ተብሏል።
እንደ ዳዊት መስፍን ዘገባ ባለፈው በጀት አመት ከቡና ወጪ ንግድ 718 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱ ይታወሳል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር