በሀዋሳ ከተማ በህይወት ማጥፋት ወንጀል ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው የብሉ ናይል ሆቴል ባለቤት በቁጥጥር ስር ዋለ

በሀዋሳ ከተማ ከአስር ቀን በፊት የሰው ህይወት አጥፍቷል ተብሎ በተጠረጠረበት ወንጀል ሲፈለግ የነበረው የብሉ ናይል ሆቴል ባለቤት አቶ ታምራት ሙሉ ሰሞኑን ከቁጥጥር ስር ውለዋል።
ግለሰቡ መስከረም 28 ረቡዕ ጠዋት ሁለት ሰአት ከ15 ገደማ በሀዋሳ መሀል ከተማ አንድ ጠበቃ ሽጉጥ ተኩሶ ህይወቱን በማጥፋትና ሌላኛውን አቁስሏል በሚል ነው የተጠረጠረው።
ወንጀሉን ፈጽሞ ተሸሽጎ ነበር የተባለው ተጠርጣሪ ከከተማው መሰወሩን ተከትሎ የክልሉ ፖሊስ ከአዲስ አበባ፣ ከፌደራልና ከክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ጋር በመተባበር ፍለጋ ሲያካሂድ ቆይቶ ነው፤
ሰሞኑን በቁጥጥር ስር መዋሉን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሀ ጋረደው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት።
ግለሰቡ ከሀዋሳ ከወጣ በኋላ አዲስ አበባ፣ባህር ዳር ፣ሚሌና ወሎን አቋርጦ ከሀገር ለመውጣት ሞክሮ ሳይሳካለት ቀርቷል።
በዚህም ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ሌላ የማምለጫ መንገድ ሲፈልግ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።
የትኛውም ግለሰብ ወንጀል ፈጽሞ ከሀገር ለመኮብለል ቢሞክር በጸጥታ ሀይል ቁጥጥር ስር እንደሚውል ከተጠርጣሪው ታምራት ሙሉ ሊማር ይገባልም ብለዋል ኮሚሽነሩ።
ግለሰቡ መያዙን ተከትሎም ምርመራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።
የወሬው ምንጭ ኤፍ.ቢ.ሲ ነው

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር