ሞሮኮ ኢቦላን በመፍራት የአፍሪካ ዋንጫን እንደማታዘጋጅ ተገለጸ

ከወራት በኋላ የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት በዝግጅት ላይ የነበረችው ሞሮኮ ኢቦላ በአፍሪካ አህጉር እያሳየ የመጣውን ከፍተኛ መስፋፋት በመፍራት ራሷን ከአዘጋጅነት ማግለሏን ዘጋርድያን አስነበበ፡፡
ደቡብ አፍሪካ፣ ግብጽ፣ ጋና  ወይም ሱዳን ውድድሩን የማዘጋጀት ዕድል አላቸው ተብሏል፡፡
ሞሮኮ ከዚህ ውሳኔዋ በፊት የጨዋታው ጊዜ ይራዘምልኝ ጥያቄ ለካፍ ማቅረቧ ይታወሳል፡፡ ምንም እንኳ ካፍ ጥያቄውን ውድ ቢያደርገውም፡፡
ሞሮኮ አላዘጋጅም ማለቷን ተከትሎ ውድድሩ ወደ ሚቀጥለው ዓመት ይራዘማል፣ ወይም ደግሞ ውድድሩ ታጥፎ በጎርጎሮሲያኑ 2017 ሊካሄድ ይችላል ተብሏል፡፡
ሞሮኮ ለሀገሪቱ ዜጎች ሲባል ከአዘጋጅነቷ ራሷን ማግለሏን የሚገልጽ ዘገባ ሱፐር ስፖርት ባለፈው ማክሰኞ  የሀገሪቱን እግር ኳስ ፌደሬሸን በማነጋገር ያወጣውን ዘገባ ዘጋርዲያን እንደ ማስረጃነት አቅርቧል፡፡
በዘገባው የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሞሀመድ ኦዚኒ እንዳሉት  አሁን ታሪካዊ ሀላፊነት አለብን፣ በውሳኔው ካፍ ችግር እንደሚገጥመው እንገነዘባለን፣ ነገር ግን በታሪክ እንደዚህ ዓይነት መጥፎ በሽታ አጋጥሞን አያውቅም ብለዋል፡፡
የ2013 የአፍሪካ ዋንጫ ያዘጋጀችው ደቡብ አፍሪካ ውድድሩን ወደ ሀገሯ ለመውሰድ ድርድር ላይ መሆኗን ዘገባው አስቀምጧል፡፡
የጋና ስፖርት ሚንስትርም ውድድሩን በሀገራቸው ለማዘጋጀት ጥያቄውን ለካፍ ለማቅረብ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡
ሞሮኮ ይህን ውሳኔ መወሰኗን ተከትሎ ካፍ ብሔራዊ ቡድኗንና ክለቦቿን ከውድድር እንደሚያግዳቸው ይጠበቃል፡፡

Source: www.ertagov.com

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር