ደኢህዴን በኣጼ ምኒልክ ላይ የሰራው ዶክመንተሪ ብኣዴንን ኣስኮርፏል ተባለ

ደኢህዴን በአጼ ምኒልክ ላይ የሰራው ዶክመንተሪ ኢህአዴግ ውስጥ ቅራኔ ፈጠረ * • በርካታ የብአዴን ካድሬዎች በሰንደቅ አላማ በዓል አልተገኙም

የደኢህዴን 22ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ተከትሎ በፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ‹‹ጮራ ፈንጣቂው ጉዟችን›› በሚል የተሰራውና አጼ ምኒልክ የደቡብ ህዝቦች ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ እንደፈጸሙ የሚሳየው ዶክመንተሪ በዴኢህዴንና በብአዴን መካከል አለመግባባት መፍጠሩን አንድ ከፍተኛ የብአዴን ካድሬ ነገረ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡
ዶክመንተሪውን ተከትሎ የብአዴን ፖለቲከኞች ኢህአዴግ በተለይም የዶክመንተሪው አዘጋጅ ደኢህዴን ላይ ተቃውሞ ያስነሱ ሲሆን ‹‹በአንድ በኩል ምኒልክ ይወደሳል፡፡ በአንድ በኩል ደግሞ ይወገዛል፡፡ ፒያሳ ላይ ያለው ሀውልት ምኒልክ መልካም ነገር እንደሰሩ ለማሳየት የተሰራ ነው፡፡ እንዲህ የምታወግዙት ከሆነ ለምን ፒያሳ የሚገኘውን ሀውልቱንስ አታነሱትም?›› በማለት በህዝብ መካከል ግጭት ይፈጥራል ያሉት መቀስቀሻ ዶክመንተሪ ላይ ተቃውሟቸውን ማንሳታቸውን የብአዴን ከፍተኛ ካድሬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
የብአዴን ካድሬዎች ዶክመንተሪውን ባዘጋጀው ደኢህዴንም ሆነ ኢህአዴግ ላይ ባላቸው ቅሬታ የዛሬው የሰንደቅ አላማ በዓል ላይ እንዳልተገኙ ተገልጾአል፡፡ በዶክመንተሪው ምክንያት በኢህአዴግ አንዳንድ ፖሊሲዎች ላይ ጥያቄ ያነሱ ሲሆን ለአብነት ያህልም እስካሁን አንስተውት የማያውቁትንና ሰንደቅ አላማው ላይ ያለው ኮከብ ላይ ጥያቄ ማንሳታቸውን የብአዴኑ ካድሬ ገልጾዋል፡፡
በቅርቡ አጼ ምኒልክን በመኮነን ከተላለፈው ዶክመንተሪ በተጨማሪ ተማሪዎች፣ ለሰራተኞችና ለሌሎች የህብረተሰብ ክፍል በተሰጠው ስልጠና ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ ታሪክ ነክ ወቀሳዎች የአብአዴን ካድሬዎች በደኢህዴንና ኢህአዴግ ላይ ላነሱት ተቃውሞ በተጨማሪ ምክንያትነት ተነስቷል፡፡
የወሬው ምንጭ www.zehabesha.com ነው

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር