መንግስት በምቀጥለው ኣመት እንደባብሎን ግንብ በግንባታ ላይ ያረጁትን የኣዋዳ ቦርቻ ኣይነት የንጽህ ውሃ ፕሮጀክቶችን ለመጠናቀቅ ማሰቡ ለህዝብ ጠቀሜታ ሲባል ነው ወይስ ለፖለቲካ?

መንግስት በምቀጥለው ኣመት እንደባብሎን ግንብ በግንባታ ላይ ያረጁትን የኣዋዳ ቦርቻ ኣይነት የንጽህ ውሃ ፕሮጀክቶችን ለመጠናቀቅ ማሰቡ ለህዝብ ጠቀሜታ ሲባል ነው ወይስ ለፖለቲካ? 


የተጀመሩ የመጠጥ ውሃ ፕሮ ጀክቶች እንዲጠናቀቁ በኣዲሱ ኣመት ርብርብ እንደምደረግ የመንግስት ሃላፊዎች ሰሞኑን ሲናገሩ ተሰምቷል፤ ለመሆኑ በሲዳማ ዞን ውስጥ ከተጀመሩ በርካታ ኣመታትን ያስቆጠሩ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዳለው የባብሎን ግንብ ታሪክ በግንባታ ላይ ያረጁ እንደ ኣዋዳ ቦርቻ ፕሮጀክትን ጨምሮ  ሌሎች በርካታ ከምገባው በላይ የተጓተቱ የንጽሕ ውሃ ፕሮ ጀክቶችን ይጨምር ይሁን? ወይስ ምርጫ ለማሸነፍ የምደረግ የገዥው ፓርቲ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ነው? ለማንኛውም በቆይታ የምናገው ይሆናል።


ሙሉ ዜናው የፋና ብሮድካንቲን ነው ፦
   

የተጀመሩ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ በአዲሱ አመት ርብርብ ይደረጋል - አቶ አለማየሁ ተገኑ

 
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 4፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት አራት ዓመታት ከ30 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል አለ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር።
በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ 5 ዓመታት 32 ሚሊዮን ህዝብ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ የታቀደ ሲሆን፥ ይሄንንም በተያዘው የ2007 በጀት ዓመት ለማሳካት ይሰራል ብለዋል ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ።
ተጠቃሚዎች በበኩላቸው የአገልግሎት ጥራት መጓደል ችግር በሰፊው እንደሚታይ ያነሳሉ።
ሚኒስትሩ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንዳሉት፥ የችግሩ መንስኤ ተለይቶ ለመፍትሄው ርብርብ እየተደረገ ነው።
የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎትን ለማሻሻል እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እንዳሉ ሆነው ፤ በከተሞች አካባቢ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የውሃ ብክነት ለመቀነስና ለመቆጣጠርም ፤ የውሃ ብክነት ቅነሳ ፕሮጀክት ተቀርጾ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች እየተተገበረ ነው ብለዋል።
ህብረተሰቡ በሁሉም ስራዎች ላይ ከሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ጋር ተቀራርቦ መስራት ከቻለም፤  የታቀዱት ስራዎች እንደሚሳኩ እምነታቸውን ገልፀዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር