ወራዊው ኣጠቃላይ ኣገራዊ የዋጋ ግሽበት በኣማካይ ጥማሪ ኣሳይቷል ተባለ

ሰሞኑን ማዕከላዊ ስታቲሰቲክስ ኤጀንሲ የወጣው መረጃ እንደምያሳየው፤ የነሐሴ ወር አጠቃላይ አገራዊ የዋጋ ግሽበት በአማካይ 7 ነጥብ 2 በመቶ ደርሷል

እንደኤጄንሲው ከሆነ፤ የሐምሌ ወር የዋጋ ግሽበት 6 ነጥብ 9 በመቶ ነበረ ሲሆን የነሐሴ ወር 2006 .ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ከሐምሌ ወር ጋር ሲነፃፀር የ 0 ነጥብ 3 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
የዋጋ ግሽበቱ ልጨምሪ የቻለው በዋናነት ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ላይ በታየው ጭማሪ ነው ተብሏል
እንደ ሬድዮ ፋና ዘጋባ ከሆነ፤ በሐምሌ ወር 5 ነጥብ 7 በመቶ የነበረው የምግብ ነክ ሸቀጦች ዋጋ የመጨመር አዝማሚያ በተጠናቀቀው የነሐሴ ወር ወደ 5 ነጥብ 2 በመቶ ዝቅ ብሏል።
በአንጻሩ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች ዋጋ የመጨመር አዝማሚያ በሐምሌ ወር ከነበረው 8 ነጥብ 2 በመቶ በነሐሴ ወር ወደ 9 ነጥብ 4 በመቶ ከፍ ብሏል።
በዚህም መሰረት የነሐሴ ወር 2006 .ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በአማካይ 7 ነጥብ 2 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።
አገራዊ የዋጋ ግሽበት ላስፐርስ በተባለ ዓለም አቀፍ ቀመር የሚለካ ሲሆን፥ ሲዳማን ጨምሮ በመላ አገሪቱ ባሉ 25 የኤጀንሲው ቅርንጫፎች አማካይነት ከ119 የገበያ ቦታዎች የዕቃዎችን ዋጋ በማሰባሰብና ወደ ዋናው ቅርንጫፍ በማምጣት በባለሙያዎች ተተንትኖ በየወሩ ይፋ እንደምያደርግ ከሮይተርስ እና ፋና ብሮ ድ ካስት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር