የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአርሶ አደሮች የመስክ በዓል አከበረ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ኘ/ጽ/ቤት ከዩኒቨርሲቲው 6 የቴክኖሎጂ መንደሮች አንዱ በሆነው በቦርቻ ወረዳ በይርባ ጋንገሶ እና ሰኒዶሎ ሊዎ ቀበሌዎች ለሚገኙ አርሶ አደሮች 11 አይነት የቦቆሎ ዝርያዎችን በተቋቋሙት የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛ ማዕከላት ላይ ሌሎች ለሚመለከታቸው አካላት በተገበት የምርምር ውጤቶቹን አስጎብኝቶአል፡፡

ነሐሴ 17­/2006 ዓ.ም በተካሄደው ስክ በዓል ላይ ከሁለቱ ቀበሌዎች የተወጣጡ ከ 80 በላይ አርሶ አደሮች የተገኙ ሲሆን ሁሉንም አይነት የቦቆሎ ዝርያዎችን በተዘጋጀው የሙከራ ጣቢያ ላይ በመዘዋወር ጎብኝተው ገምግመዋል፡፡ ከግምገማው በኃላ ሊሙ ሻላ ጊቤ1 እና መልካሳ የተባሉት የበቆሎ ዝርያዎች ለአከባቢው ሥነ ምህዳር አመቺ በሰብል አያያዛቸው የተሻሉና በምርታማነታቸው በአርሶ አደሩ የተመረጡ ናቸው ፡፡
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ኘ ዶ/ር ተስፋዬ  እንደተናገሩት ለሙከራ ከተዘሩት 11 አይነት የቦቆሎ ዝርያዎች መካከል ለአከባቢውና ለወረዳው ሥነ ምህዳር ተስማሚ የሆኑትን መለየትና በቀጣይም ከወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለአርሶ አደሩ እንዲዳረሱ ማድረግ የበዓሉ ዋነኛ አላማ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ኘ/ጽ/ቤት በተመረጡ የቴክኖሎጂ መንደሮች አርሶ አደሩን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡
በበአሉ ላይ አቶ ሚንጃ ሀይሶ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ተወካይና  የሰብል ልማት ኤክስቴንሽን ሥራ ሂደት አስተባባሪን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው የበላይ አመራር አካላት፣ የወረዳው ግ/ጽ/ቤት ተወካዮች፣  የሰብል ልማት ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች  ፣ ተመራማሪዎችና አርሶ አደሮች ተሳትፈዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር