አቶ አዲሱ ሃባ የደቡብ ግሎባል ባንክ ፕሬዚዳንት ሆኑ

ከአቢሲኒያ ባንክ ፕሬዚዳንትነታቸው የለቀቁት አቶ አዲሱ ሃባ የደቡብ ግሎባል ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቀደ፡፡
አቶ አዲሱ ከአቢሲኒያ ባንክ በቅርቡ ከለቀቁ በኋላ የደቡብ ግሎባል ባንክ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ባንኩ ለብሔራዊ ባንክ ባመላከተው መሠረት፣ ሹመታቸውን በማፅደቁ ሥራቸውን በይፋ መጀመራቸው ታውቋል፡፡
አቶ አዲሱ ከአቢሲኒያ ባንክ የሥራ መልቀቂያ በማስገባት የተሰናበቱ ሲሆን፣ አቢሲኒያ ባንክም 500 ሺሕ ብር ሸልሟቸው እንደሸኛቸው ይታወሳል፡፡ 
የአቶ አዲሱን ሹመት እንዲቀበል የደቡብ ግሎባል ባንክ ብሔራዊ ባንክን በደብዳቤ ከመጠየቁ ቀደም ብሎ፣ የደቡብ ግሎባል ባንክን በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ወርቁ ለማ ከሥራ መልቀቃቸው መዘገባችን አይዘነጋም፡፡ 
አቶ ወርቁ ከኃላፊነት መነሳት በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ነው ቢባልም፣ አንዳንድ ወገኖች ግን ከቦርዱ ጋር በተፈጠረ ያለመግባባት ነው ይላሉ፡፡ ብሔራዊ ባንክ እንዲህ ያሉ ሹመቶችን ለማፅደቅ ጊዜ የሚወስድበት ቢሆንም፣ የአቶ አዲሱን ሹመት ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አፅድቆታል፡፡ 
አቶ አዲሱ ከአቢሲኒያ ባንክ በለቀቁ በጥቂት ሳምንት ልዩነት የሌላ ተፎካካሪ ባንክ ፕሬዚዳንት መሆናቸው፣ በባንክ ኢንዱስትሪው ውስጥ የባለሙያዎች መነጣጠቅን ያሳያል የሚል አስተያየትም የሚሰጡ አሉ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ አዲሱ የደቡብ ግሎባል ባንክ ፕሬዚዳንት በመሆናቸው ምክንያት የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ፕሬዚዳንትነታቸውን እንዲቀጥሉ ያስችላቸዋል፡፡   

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር