ኣዲሱን ኣመት ምክንያት በማድረግ የደቡብ ክልል ብሎም የሲዳማ ዞን መንግስት ለሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፤ ኢትዮጵያ በእስረኞች ቁጥር በኣፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች

ሰሞኑን ከኣገሪቱ መገናኛ ብዙሃን የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈጸማቸው የእስራት ቅጣት ውሳኔ ተላልፎባቸው ሁለት ሦስተኛውን የቅጣት ጊዜያቸውን በእስራት ያሳለፉና በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ሥነ ምግባር የነበራቸው፣ ከ900 በላይ ታራሚዎች ኣዲሱን ኣመት ምክንያት በማድረግ በይቅርታ እንደሚፈቱ ገልጸዋል፡፡

Photo from http://mereja.com/forum/viewtopic.php?t=70171&p=427589
እንደሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ታራሚዎቹ ስለይቅርታ አጠያየቅ በይቅርታ ቦርድ ጽሕፈት ቤት በተዘጋጀው ቅጽ መሠረት ሞልተው የሚያቀርቡትን የይቅርታ ጥያቄ፣ ቦርዱ ተቀብሎና ከማረሚያ ቤቶቹ አጣርቶ ለፍትሕ ሚኒስቴር ካቀረበ በኋላ፣ ሚኒስቴሩ ለአገሪቱ ፕሬዚዳንት በማቅረብ ፕሬዚዳንቱ ይቅርታ እንደሚያደርጉ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በይቅርታ ቦርድ ጽሕፈት ቤት በኩል ተጣርቶ የቀረቡላቸውን ከ900 በላይ ታራሚዎች፣ ከእስር እንዲለቀቁ ጳጉሜን 5 ቀን 2006 .. ይፋ እንደሚያደርጉ ተገልጿል፡፡

እነዚሁ ታራሚዎች በኣዲሱ ኣመት ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንድቀላቀሉ ለማድረግ መታሰቡ ይበል የሚያሰኘ ኣካሄድ ቢሆንም በኣገሪቱ ውስጥ በእስር ላይ ከምገኙ በርካታ ቁጥር ካላቸው ታራሚዎች ኣንጻር በይቅርታ የምፈቱት ታራሚዎች ቁጥር በጣም ኣነስተኛ ነው።

ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች እንደምያሳዩት በኢትዮጵያ ሶስት ፌደራል ፤ ከ117 በላይ የክልል እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ያልታወቁ እስር ቤቶች እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን፤ ኣለምኣቀፍ የእስረኞች ጥናት ማዕከል (InternationalCentre for Prison Studies – ICPS) ከኣንድ ኣመት በፊት ባሳተመው World Prison Population List ኣስረኛው እትም ላይ እንዳስቀመጠው እንደፈረንጆቹ ዘመን ኣቆጣጠር ከ2009 እስከ 2010 በኢትዮጵያ ከ112 ሺ በላይ እስረኞች በተለያዩ እስር ቤቶች ይገኙ ነበር፤ ይህ ቁጥር ኣገሪቷን ከደቡብ ኣፍሪካ ቀጥሎ በርካታ የእስረኞች ቁጥር በመያዝ በኣፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ኣስቀምጧታል።
ሰለእስር ቤቶቹ ኣያያዝ በተመለከተ በዊኪፔዲያ እንደምከተለው ተብሏል፦
Prison conditions have been reported as unsanitary and there was no budget for prison maintenance. Medical care was unreliable in federal prisons and almost nonexistent in regional prisons. The daily meal budget was approximately 5 Birr (50 cents) per prisoner, and many prisoners supplemented this with daily food deliveries from their family or by purchasing food from local vendors. Prisoners often had less than 22 square feet (2.0 m2) of sleeping space in a room that could contain up to 200 persons; sleeping in rotations was not uncommon in regional prisons.
የሆነ ሆኖ የደቡብ ክልል ብሎም የሲዳማ ዞን መንግስት እየፋመ በሚበርደው የዞኑ የፖለቲካ ትኩሳት የተነሳ በየጊዜው በጅምላ በእስር ቤት ያጎራቸውን በኣገሪቱ ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 28 የተዘረዘሩትን የወንጀል ዓይነቶች ማለትም የሰው ዘር ማጥፋት ወንጀል፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት ዕርምጃ መወሰድ፣ አስገድዶ ሰውን መሰወር፣ ኢ-ሰብዓዊ የድብደባ ወንጀሎችን ያልፈጸሙ፣ ከተፈረደባቸው የእስር ጊዜ ከሁለት ሦስተኛ በላይ የታሰሩና በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ሥነ ምግባር ለነበራቸው የሲዳማ ታራሚዎች ይቅርታ በማድረግ ከእስር ቢፈታ መልካም ነው፡፡


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር