የሲዳማ ማክሮ ፋይናንስ ባለፉት 15 ኣመታት ተቀማጭ ካፒታሉን ከ200ሺ ብር ወደ ሁለት ሚሊዮን ዶላር ማሳደግ ብችልም፤ በዞኑ የማክሮ ፋይናንስ ገበያ ያለው ተወዳዳሪነት እየቀነሰ ነው


እንደፈረንዶቹ ዘመን ኣቆጣጠር በ1998 ኣመተምህረት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነገር ግን ሰርተው መለወጥ የምችሉ፤ በገጠር እና ከተማ ነዋሪ የሆነው እና ኣማራጭ የገንዘብ ተቋማት በኣቅራቢያቸው የሌሏቸው ዜጎች ለመረዳት ተብሎ በ200ሺ ብር ካፒታል የተቋቋመው የሲዳማ ማክሮ ፋይናንስ ባለፉት 15 ኣመታት ተቀማጭ ካፒታሉን ወደ ሁለት ሚሊዮን ዶላር ማሳደግ ብችልም፤ በዞኑ የማክሮ ፋይናንስ ገበያ ያለው ተወዳዳሪነት እየቀነሰ ነው።

  • የማክሮ ፋይናሱ ኣሴት ( Assets) ባለፉት ኣስርተ ኣመታት ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ወደ 1ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ወርዷል፤
  • የማክሮ ፋይናንሱ ኤኪቲይ ( Equity) ደግሞ ከ1 ነጥብ9 ሚሊዮን ዶላር ወደ 619 085 06 ሳንቲም ወርዷል፤
  • ግሮስ ሎን ፖርትፎልዮ ( Gross Loan Portfolio) ደግሞ ከ 657678 99 ሳንቲም ወደ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ኣድጓል፤

ቀድሞ የሲዳማ ልማት ፕሮግራም በኃላ ላይ ደግሞ የሲዳማ ልማት ኮፕሬሽን እህት ኩባንያ ሆኖ በፍቃድ በቁጥር 40/1996 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቁጥጥር ስር ሆኖ የተመዘጋበው የሲዳማ ማክሮ ፋይናንስ በሲዳማ ዞን ውስጥ ባሉ የገጠር እና ከተማ ቀበሌያች የብድር ኣገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆን ወደ 50 ሺ የሚጠጉ የኣገልግሎቱ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ታውቋል።

ከኤም ኤፍ ኣይ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ማክሮ ፋይናንሱ እኣኣ በ2012ኣም 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ግሮስ ሎን ፖርትፎሊዮ ሲኖረው፤ በኣማካይ 51 ነጥብ 8 ዶላር ማለትም ወደ ኣንድ ሺ ብር ለየኣንዳንዱ ተበዳር ኣበድሯል።

የማክሮ ፋይናንሱ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ኣለው።

ለተጨማሪ መረጃ፦ mixmarket.org

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር