ብሔራዊ ሊግ የሚቀላቀሉ ክለቦችን ለመለየት ከመጪው ሃሙስ ጀምሮ ውድድር ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በቀጣዩ አመት ወደ ብሔራዊ ሊግ የሚቀላቀሉ ክለቦችን ለመለዬት ከመጪው ሃሙስ ጀምሮ በሃዋሳ ከተማ ውድድር ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ውንድምኩን አላዩ እንደገለጹት፥ በቀጣዩ ዓመት ወደ ብሔራዊ ሊግ የሚቀላቀሉ ስምንት ክለቦችን ለመለየት ከዘጠኙ ክልሎች እና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 31 ክለቦች በውድድሩ ተሳታፊ ይሆናሉ።
አማራ፣ ደቡብ፣ ኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች እንዲሁም የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳድሮች እያንዳንዳቸው አራት ክለቦችን ያሳተፋሉ፡፡
የአፋር እና የቤንሻንጉል ጉምዝ  ክልሎች ደግሞ እያንዳንዳቸው ሁለት ክለቦችን የሚያሳትፉ ሲሆን፥ ጋምቤላ፣ ሐረር እና ሶማሌ ክልል እያንዳንዳቸው በአንዳንድ ክለቦች ይወከላሉ።
ውድድሩ ከሃሙስ ጀምሮ እስከ ነሐሴ 25 ቀን ድረስ ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ ውድድር ከዋናው ፕሪሚየር ሊግ ቀጥሎ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ውድድር ሲሆን 69 ክለቦችን የሚያሳትፍ ነው።
ምንጭ፦ ኢዜአ
_____________________________________________________________
We welcome comments that advance the story through relevant opinion and data. If you see a comment that you believe is irrelevant or inappropriate, please! inform us. The views expressed in the comments do not represent those of Bloggers.

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር