የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ጉባኤ በጀትና ደንቦችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ

ሀዋሳ ሐምሌ 27/2006 የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በጀትና ሁለት ደንቦችን በማፅደቅ ትናንት ማምሻውን ተጠናቀቀ፡፡
ምክር ቤቱ በትናንትናው ውሎ የሃዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2006 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት በማድረግ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል፡፡
በተለይ በከተማ ቀልጣፋና ውጤታማ የፍትህ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች በተጨማሪ አዳዲስ ምድቦችንና ተዘዋዋሪ ችሎሎቶች በመክፈት የተከናወኑ ስራዎች አበረታች በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ምክር ቤቱ አሳስቧል፡፡
ምክር ቤቱ በ2007 በጀት አመት ለመደበኛና ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጽድቋል፡፡
በጀቱ የሚሸፈነው ከመንግስት ግምጃ ቤት፣ ከከተማ ገቢ እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ፣ ከጤናና ትምህርት ተቋማት ገቢ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
በከተማው የሚከናወኑ የመልካም እስተዳደር፣ የልማትና ዴሚክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የተመደበው በጀት ካለፈው በጀት አመት ጋር ሲነጻጸር  ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው ነው፡፡
የምክር ቤቱ ጉባኤ በተጨማሪም የሃዋሳ ሀይቅን እንዲሁም ተራራማና ረግረጋማ መሬት አያያዝና አጠቃቀምን ለመወሰን የወጣውንና  የስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ስነ ሰርዓት ረቂቅ ደንቦች ላይ ከተወያየ በኋላ በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል፡፡
Source: ENA
________________________________________________________

We welcome comments that advance the story through relevant opinion and data. If you see a comment that you believe is irrelevant or inappropriate, please! inform us. The views expressed in the comments do not represent those of Bloggers.

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር