ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ከምትልከው ቡና የምታገኘው ገቢ በ25 በመቶ እንደሚያድግ እየተነገረ ነው፤ 1/3ኛውን የቡና ምርት ኣቅራቢ የሆኑትን የሲዳማ ቡና ኣምራቾችን ተጠቃሚ ለማድረግ ምን ታስቧል?


አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 15፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) ኢትዮጵያ በ2014/15 ወደ ውጪ ከምትልከው የቡና ምርት ከ900 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ልታገኝ እንደምትችል ተገለጸ።
ይህም ቀደም ሲል ከነበረው ገቢ የ25 በመቶ እድገት ያሳየ ነው ተብሏል።
የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አለምሰገድ አሰፋ እንደተናገሩት፥ በያዝነው አመት የብራዚል ቡና በድርቅ በመመታቱ የቡና ዋጋ መሻሻል አሳይቷል።
በዚህም አሁን በገበያ ላይ ያለው የቡና ዋጋ ባለበት ሊቀጥል እንደሚችል ነው አቶ አለምሰገድ የጠቆሙት።
ዋነኛዋ ቡና አምራች ሀገር ብራዚል ባስተናገደችው ድርቅ የተነሳ አቅርቦቷ መቀነሱን ተከትሎ፥ ኒውዮርክ እስከ ጥር ወር ድረስ 70 በመቶ የቡና ፍላጎትን ከኢትዮጵያ በመግዛት ስትሸፍን መቆየቷም ተዘግቧል።
በአፍሪካ ቀዳሚዋ ቡና አምራች ሀገር ኢትዮጵያ፥ ባለፉት 12 ወራት ወደ ውጪ ከላከችው ቡና 719 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያገኘች ሲሆን ፥ ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፃር በ3 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ያለ ነው።
ሀገሪቱ በዚህ አመትም ከ500 ሺህ ቶን በላይ ቡና ታመርታለች ተብሎ ይጠበቃል ያሉት ስራ አስኪያጁ፥ ከአጠቃላይ ምርቱ ግማሽ ያህሉም ለውጭ ገበያ እንደሚቀርብ ተናግረዋል።
የቡና አምራች አካባቢዎች መስፋፋት ለምርቱ ማደግ አስተዋፅኦ ያደርጋልም ነው ያሉት።
በሼክ ሙሃመድ አላሙዲ የሚተዳደረው የሆራይዘን ፕላንቴሽን፥ 10 ሺህ ሄክታር  በበበቃ እንዲሁም 12 ሺህ 114 ሄክታር የቡና እርሻ መሬት መግዛቱን አስታውሶ የዘገበው ብሉምበርግ ነው።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር