ኢትዮጵያ የ2017ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ጥያቄ ልታቀርብ ነው

ኢትዮጵያ የ2017ቱን የአፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ ፍላጎት አላት አሉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ።
የሊቢያን ውድድሩን ከማስተናገድ መታገድ ተከትሎ ነው ኢትዮጵያ ይህን አህጉራዊ የእግር ኳስ ውድድር ለማዘጋጀት ፍላጎት ያሳየችው።
ፕሬዚዳንቱ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፥ ኢትዮጵያ  የ2017ቱን የአፍሪካ ዋንጫ  ለማስተናገድ ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት አላት።
ለዚህም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከጎናቸው እንዲቆም ነው አቶ ጁነዲን የጠየቁት።
የአዲስ አበባ ስታዲየምን ጨምሮ ከ80 በመቶ በላይ የተጠናቀቀው የባህር ዳር ስታዲየም እና በመቀሌ እና በሀዋሳ በመገንባት ላይ ያሉት ሰታዲየሞች በመፋጠን ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
ኬኒያም ከታንዛኒያ፣ ሩዋንዳ አልያም ኡጋንዳ ጋር በመጣመር ውድድሩን ለማስተናገድ ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች።
ከሱዳን እና ግብፅ ጋር በመሆን የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫን የመሰረተችው ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ1962፣ 1968 እና 1976 ውድድሩን አስተናግዳለች።
የአፍሪካ እግር ኳስ ማህበርም የ2017ቱን የአፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጅ ሀገር በፈረንጆቹ 2015 የሚያሳውቅ ይሆናል።
ዜናው የኤፍ.ቢ.ሲ.ነው

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር