የሃዋሳ መምራን ትምህርት ኮሌጅ ለሁለተኛ ጊዜ በሲዳማ ኣፎ ያሰለጠናቸውን መምህራን ኣስመረቀ

የሃዋሳ መምራን ትምህርት ኮሌጅ ለሁለተኛ ጊዜ በሲዳማ ኣፎ ያሰለጠናቸውን መምህራን ኣስመረቀ ሰሞኑን  ኣስመርቋል። ዝርዝር ዜናው የኢዜኣ  ነው

የሃዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ከ1ሺህ 300 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ

ሀዋሳ ሰኔ 29/2006 የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ የለውጥ አንቀሳቃሽ በመሆን የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን የሃዋሳ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ አንዳንድ ተመራቂ ተማሪዎች ገለጹ፡፡
ኮሌጁ ከ1ሺህ 300 በላይ ተማሪዎችን በመምህርነት ሙያ አሰልጥኖ ትናንት አስመረቋል፡፡
ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል መሃመድ ሳኒ፣ ጥበቡ እንግዳና ዳዊት ዳንኤል እንዳሉት መምህርነት ከራስ ይልቅ ለሌላው መኖርን የሚጠይቅ ክቡር ሙያ ነው፡፡
በመሆኑም የለውጥ አንቀሳቃሽ በመሆን ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት የሚጠበቅባቸው ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ህፃናት ከመጀመሪያ የትምህርት ደረጃ ጀምሮ ባሉ ሁሉም የትምህርት እርከኖች በእውቀት፣ በአመለካከትና በስነ ምግባር ታንፀው እንዲወጡ የማድረግ ስራ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡
በትምህርት ተቋም ያገኙትን እውቀት በተግባር ላይ በማዋል የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ የተጀመሩ ስራዎች ከዳር ለማድረስ ጠንክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
የሃዋሳ መምህራን ኮሌጅ ዲን አቶ አበራ አርጎ ኮሌጁ ለ16ኛ ጊዜ በመምህርነት ሙያ አስልጥኖ ያስመረቃቸው ከ1ሺህ 300 በላይ ተማሪዎች በመደበኛ፣ በማታና በክረምት ፕሮግራም ለሶስት ዓመታት በዲፕሎማና በትምህርት አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ኮሌጁ የዘንድሮን ተመራቂዎች ጨምሮ ባለፉት 16 ዓመታት በተለያዩ የዲፕሎማ መርሀ ግብር 30ሺህ 244 መምህራንን አሰልጥኖ በማውጣት  ለክልሉ የትምህርት ልማት አስተዋጽኦ ማድረጉን መልክተዋል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ማቴዎስ ማልዳዬ ከየትምህርት ክፍሉ ክፍተኛ ውጤት ላመጡ ተመራቂ ተማሪዎች የሜዳሊያ ሽልማት ሰጥተዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር