የደመወዝ ማስተካከያ ዝርዝር ይዘት በቅርቡ ይፋ ይሆናል ተባለ፤ የደሞወዝ ጭማሪውን ተከትሎ ሃዋሳን ጨምሮ በኣንዳንድ የሲዳማ ከተሞች በሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል

ለመንግስት ሠራተኛው የተደረገው የደመወዝ ማስተካከያ ዝርዝር ይዘት በመጪዎቹ ሁለት ሣምንታት ይፋ እንደምሆን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።መገናኛ ብዙሃኑ የመንግስት ከፍተኛ የሰራ ሃላፊን ጠቅሰው እንደዘጋቡት፤ መንግስት የሲቪል ሠራተኛውን ኑሮ ለማሻሻል ከወሰዳቸው እርምጃዎች መካከል የደመወዝ ማስተካከያ በዋነኝነት ተጠቃሽ መሆኑን ነው። 

በአሁኑ ወቅት የደመወዝ ማስተካከያው ዝርዝር ሥራ በመከናወን ላይ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ይፋ እንደሚሆን ገልጸዋል።
አስፈላጊ ሥራዎች ከተጠናቀቁ የተደረገው የደመወዝ ማስተካከያ ከሐምሌ ወር 2006 .ም ጀምሮ ለሠራተኛው የሚከፈል መሆኑን ታውቋል
በተመሳሳይም የመንግስት ሠራተኛውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ እየተገነቡ ካሉት የጋራ መኖሪያ ቤቶች የ20 በመቶ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ የመንግስት መገናኛ ብዙሃኑ አመልክተዋል።
ኣክለውም የሠራተኛውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍም በፌዴራል ደረጃ ለዚሁ አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎች እየተመረቱ መሆኑንና በቅርቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ አስረድተዋል።
አንዳንድ ነጋዴዎች የደመወዝ ማስተካከያውን ተከትሎ በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ መንግስት የተለያዩ የቁጥጥር ሥራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል።
በሌላ በኩል መሰረታዊ የሚባሉ ሸቀጦችን በ "አለ በጅምላ" ድርጅት በኩል በማቅረብ ኅብረተሰቡ ሸቀጦችን ፍትሃዊ በሆነ ዋጋ እንዲያገኝ የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱን ጠቅሰዋል።
የደመወዝ ማስተካከያው ኢኮኖሚው ተረጋግቶ መቀጠል በሚችልበትና የኑሮ ውድነትን በማያባብስ መልኩ ተጠንቶ ተግባራዊ የሚደረግ እንደሆነም ገልጸዋል።
ባለፈው ሰኔ 16 ቀን 2006 .ም በአገር አቀፍ ደረጃ ለ8ኛ ጊዜ በተከበረው የሲቪል ሰርቪስ ቀን በዓል ላይ ከአዲሱ በጀት ዓመት ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው የደመወዝ ማስተካከያውን ጨምሮ የተለያዩ የኑሮ ማሻሻዎች እንደሚደረጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ መግለፃቸው የሚታወስ ነው።
ይህ በእንድህ እንዳለ፤ በሃዋሳ ከተማ እና ኣከባቢያዋ ኣንዳንድ ነጋዴዎች በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸውን ሸማቾች በመናገር ላይ ናቸው።
የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ሪፖርተር ባደረገው የገበያ ቅኝት እንዳረጋገጠው በተለይ በሃዋሳ ከተማ ገና ከኣሁኑ በሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር