ሃዋሳ ከተማ የመሰመር ካርታዋን ተረከበች

የመስመር ካርታው በሃዋሳ እና በመሰል ከተሞች በመሬት እና መሬት ነክ የመረጃ አያያዝን ዘመናዊ በማድረግ ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን ያስቀራል ተብሏል።
ዜናው የኤፍ.ቢ.ሲ፦ 
የመስመር ካርታ መዘጋጀቱ በከተሞች በመሬት እና መሬት ነክ የመረጃ አያያዝን ዘመናዊ በማድረግ ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን ያስቀራል አሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የኢንፎርሜሽን እና መገናኛ እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ዶክተር ደብረፂሆን ገብረሚካኤል።
የመስመር ካርታው የተዘጋጀላቸው በ5 ክልሎች የሚገኙ ከተሞች እና ለድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ነው።
ባህር ዳር ፣ ሃዋሳ፣ አዳማ ፣ሃረር እና ድሬደዋ ከተማ የመስመር ካርታው ከተዘጋጀላቸው ተጠቃሾች ናቸው።
ይህም ከዚህ ቀደም የነበረውን ወጥነት የሌላቸው እና እርስ በእርሳቸው የማይናበቡ እና በቀላሉ ለብልሹ አሰራር በር ከፍተው የነበሩ አሰራሮችን ያስወግዳሉ።
ከዚህም በተጨማሪ ለመጀመሪያ ግዜ በሃገር ውስጥ ባለሞያ የተዘጋጀው የመስመር ካርታ የመሬት እና መሬት ነክ መረጃዎችን ዘመናዊ ከማድረግም ባሻገር የሃገርን ደህንነት የሚያስጠብቅ ነው ተብሎለታል።
የ 23 ከተሞችን የመስመር ካርታ ለማዘጋጀት ከ 40 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን በቀጣይም የ 68 ከተሞች የመስመር ካርታ ዝግጅት ይደረጋል መባሉን በላይ ተስፋዬ ዘግቧል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር