የሲዳማ ፊቼ በኣል በማይዳሰሱ እና ኣስቸኳይ ጥበቃ በሚሹ ባህል ስር በዩኔስኮ በኣለም ቅርስነት መመዝገቡ ወይም ኣለመመዝገቡ የምታወቀው እንደፈረንጆች የዘመን ኣቆጣጠር በ2015_2016 ባለው ጊዜ ውስጥ መሆኑ ታወቀ።

© 2013 by the Authority for Research and Conservation of Cultural Heritage (ARCCH)
EN: After the actual date for the Fichee celebration is reckoned and identified by ayyanto, clan leaders and competent elder (chimeesa) attend a meeting called songo summoned to make decision on the proclamation of the date to the people.

የሲዳማ ኣዲስ ኣመት በኣል ፊቼን በኣለም የማይዳሰሱ እና ኣስቸኳይ ጥበቃ በሚሹ ባህል ተርታ መመዝገቡና ኣለመመዝገቡ የምታወቀው ከሶስት ኣመታት በኃላ ነው።

ከዩኔስኮ ድረገጽ ላይ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የፌቼን በኣል በኣለም ቅርስነት ለማስመዝገብ መሟላት ያላባቸው ዶክመንቶች እየተሟሉ ያሉ ቢሆንም፤ ሌሎች ቅዲሚያ የምሰጣቸው መሰል ቅርሶች በመኖራቸው የተነሳ የፊቼን በኣል የመመዝገቡ ሂደት ለሚቀጥሉት ሶስት ኣመታት ልቆይ ይችላል።

ለዚህም እንደምክንያት የምጠቀሰው፤ በኣለም ቅርስነት እንድመዘገቡላቸው ጥያቄ ከሚያቀርቡ ኣገራት መካከል እስከኣሁን ድረስ ምንም ኣይነት መሰል ቅርሶችን ያላስመዘጋቡ ወይም ጥቂት ቅርሶችን ያስመዘጋቡ ኣገራት እና ከ25 ሺ የኣሜሪካ ዶላር በላይ ለቅርሶች እንክብካቤ ጥያቄ ኣቅርበው ወሳኔ የተሰጣቸው ቅርሶች ቅዲሚያ እንድያገኙ በሚል በዩኔስኮ ስምምነት ኣንቀጽ 34 ላይ በተቀመጠው መሰረት ለእነዚሁ ቅርሶች በቅድሚያ እውቅና የሚሰጥ በመሆኑ ነው።

2015 እና በ2016 ውሳኔ ይሳጥባቸዋል ተብሎ በዩኔስኮ ፊይል ውስጥ የተካተቱት የማይዳሰሱ እና ኣስቸኳይ ጥበቃ በሚሹ ባህል እና ሌሎች በቁጥር 100 ሲሆኑ፤ ፊቼን ጨምሮ በ50ዎቹ ላይ በ2015 ታህሳስ ወር በሚካሄደው ጉባኤ ውሳኔ ይሰጥበታል ተብሎ ይጠበቃል።



Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር