የመንግስት መገናኛ ብዙሃን የሲኣን/ መድረክ ሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎችን ቁጥር ኣሳንሰው ዘገቡ

ከሰላማዊ ሰልፈኞቹ መካከል
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን በዛሬው እለት በሃዋሳ ከተማ የተካሄደውን የሲኣን/ መድረክ ሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎችን ቁጥር በእጅጉ ኣሳንሰው መዘገባቸው ተሰማ።

በወቅታዊው የኣገሪቱ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ድምጻቸውን ለማሰማት ወደ ኣደባባይ በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ የተመመ ሲሆን፤ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በሺዎች የምቆጠሩ ሰዎች መገኘታቸውን ከሲኣን የተገኘው መረጃ ያመክታል።

ሆኖም የመንግስት መገናኛ ብዙሃን  ይህንን ብዛት የለውን ሰላማዊ ሰልፈኛን ቁጥር በማሳነሰ የሰላማዊ ሰልፈኛውን ቁጥር ወደ 200 ኣውርደው መዘገባቸው ታውቋል።

ከመገናኛ ብዙሃኑ ዘጋባ መካከል የሚከተለውን ለኣብነት ኣቅርበነዋል፦ 

መድረክ በሀዋሳ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደ


ሀዋሳ ሰኔ 07/2006 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደ፡፡
መድረክ በዚሁ ሰልፍ ላይ የተለያዩ የተቃውሞ መፈክሮችን አሰምቷል፡፡
የመድረክ ዋና ጸሐፊ አቶ ገብሩ ገብረማርያም በሰልፉ ላይ እንዳሉት ኢህአዴግ የህግ የበላይነትን በማክበርና በማረጋገጥ ነጻ ፍትሐዊ ዴሞክራሲያዊና ታዓማኒነት ያለው ገለልተኛ የምርጫ አስተዳደር እውን እንዲሆን ማድረግ አለበት፡፡
ዜጎች ያለ ፖለቲካዊ ወገንተኝነት ከሀገራቸው ልማትና እድገት ውጤቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንጠይቃለን ብለዋል።
መድረክ የሀገሪቱን ወቅታዊና መሰረታዊ ችግሮች መፍቻ አቅጣጫ ነው ያለውን ማንፌስቶ በህዝቡ ድጋፍ ስራ ላይ እንዲውል ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጿል፡፡
በሰልፉ ላይ የተሳተፉት ሰዎች  ከ200 በላይ እንደሚገመቱ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡
ሰልፉም በሰላም መጠናቀቁን ጸጥታ አንዳንድ የጸጥታ አስከባሪዎች ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜኣ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር