በግብርና ምርቶች ላይ እሴት ጨምሮ መላክ የሚያስችል የተቀናጀ የግብርና ኢንዱሰትሪ ፓርኮች ሊመሰረቱ ነው

 በግብርና ምርቶች ላይ እሴት ጨምሮ መላክ የሚያስችል "የተቀናጁ የግብርና ኢንዱሰትሪ ፓርኮች" ለመመስረት የሚያስችል ጥናት በማካሄድ ላይ እንደሆነ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለፀ።
ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር መብራቱ መለስ የግብርና ምርቶችን እሴት ጨምሮ ወደ ውጭ ገበያ ማቅረብ እንደሚያስፈልግና ለዚህም እሴት ጨምረው መላክ የሚያስችሉ ኩባንያዎች ማቋቋም መሰረታዊ ነገር መሆኑን ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ፓርኮቹ የግብርና ምርት በብዛት የሚገኝባቸው ቦታዎችን በጥናት በመለየት የሚከናወኑ ናቸው ።
የግብርና ምርቶችን እሴት ጨምሮ ለአለም ገበያ ባለማቅረብ የተነሳ አገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እያጣች ነው ያሉት ሚኒስትሩ በቀጣይ ግን ፓርኮችን ገንብቶ ኢንዱስትሪዎች በማቋቋም  ከፍተቱን ለሞምላት እንደሚጥሩ ተናግረዋል።
የሚቋቋሙት ኢንዱሰትሪዎች የገበሬውን የግብርና ምርት በስፋት መጠቀም መቻላቸው አርሶ አደሩ ዘላቂና አስተማማኝ የሆነ የገቢ ምንጭ እንዲኖረው እንደሚያደርግና የአርሶ አደሩን ህይወት መቀየር እንደሚችሉ አስረድተዋል።
በሚቋቋሙት ኢንዱስትሪዎችም ከፍተኛ የስራ እድልና የኢንተርፕራይዞች መፈጠር እንደሚያስፋፋ ጨምረው ተናግረዋል።
ሚኒሰትሩ እንደተናገሩት "የተቀናጁ የግብርና ኢንዱሰትሪ ፓርኮች"  በስኳር ማምረቻ አካባቢዎች፣ የፍራፍሬና የአትከልት ምርት በስፋት በሚኖርባቸው፣ የሰሊጥ እንዲሁም የቡና ምርቶች በሚበዙባቸው ቦታዎች ላይ ይጀመራሉ።
በሚቀጥለው የበጀት አመት በሚጠናቀቀው የእድገትና የትራንስፎርሜሺን እቅድ ላይ መጀመር እንዲቻል የጥናት ስራው በመፋጠን ላይ ይገኛል ያሉት ሚኒሰትሩ በሚቀጥለው የእቅድ ዘመን ግን በስፋት በመላው አገሪቱ እንደሚተገበሩ አረጋግጠዋል።
ተሞክሮውን ከህንድ የተወሰደ ሲሆን በዚህም  የአብዛኛውን አርሶ አደር ህይወት በመቀር ላይ ትገኛለች ብለዋል።
ዜናው የኢዜኣ ነው

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር