የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ማስተካከያ ሊደረግ ነው

መንግስት የዋጋ ንረትን በማይቀሰቅስ ሁኔታ የተጠና የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ማስተካከያ ከሀምሌ ወር 2006 ዓ.ም ተግባራዊ እንደሚያደረግ ተሰማ።
 ለ8ኛ ጊዜ እየተከበረ ባለው የሲቪል ሰርቪስ ቀን ላይ የመንግስት ሰራተኞችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍም በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ላይ 20 በመቶ ቅድሚያ የሚያገኙበት ሁኔታ መመቻቸቱንና የትራንስፖርት ችግርንም በተመሰሳይ ለመቅረፍም የሰርቪስ አገልግሎት በየመስሪያ ቤቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መደረጉን ተነግሯል።
በሃገሪቱ የእድገት ጉዞ ውስጥ የራሱን ወሳኝ ድርሻ በመወጣት ላይ ለሚገኘው የመንግስት ሰራተኛ  የመኖርያና የትራንስፖርት ችግርን ለማቃለል የሚያስችሉ መፍትሄዎች መንግስት እንደሚያቀርብለት ተገልጿል።
በተያያዘ በሁሉም ደረጃዎች ባሉ የመንግስት መዋቅሮች ልማታዊ መልካም አስተዳደርና የላቀ የስራ አፈፃፀም በማረጋገጥ የተጀመሩትን የለውጥና የሪፎርም ስራዎች ከዳር ለማድረስ በቁርጠኝነት መሰራት ይገባል ተብሏል።
 በዚህ የሲቪል ሰርቪስ ቀን በዓል ላይ የኣገሪቱ ከፍተኛ ኣመራሮች መገኘታቸውን ወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ዘግቧል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር