ኣሰልጣኝ ባሬቶ ለብሔራዊ ቡድን ሁለት ተጫዋቶችን ከሃዋሳ ከነማ መረጡ

ዜናው የ ኢዜኣ ነው
አዲስ አበባ ሰኔ 5/2006 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ በሚቀጥለው ዓመት በሞሮኮ በሚዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ የሚካፈሉ ተጫዋቾችን መረጡ።

አሰልጣኙ ተጫዋቾቹን የመረጡት በውጭ ከሚጫወቱ ኢትዮጵያዊያንና ከሀገር ውስጥ ካሉ ከስምንት የተለያዩ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦችና ከብሄራዊ ሊግ ነው።
ከተመረጡት 38 ተጫዋቾች መካከል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን 11 ተጫዋቾችን በማስመረጥ ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል።
የደደቢት እና የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለቦች እያንዳንዳቸው ስምንት ተጫዋቾችን፣ ሀዋሳ ከነማ ሁለት፣ እንዲሁም መከላከያ፣ ናሽናል ሲሚንቶ፣ዳሽን ቢራና ሙገር ሲሚንቶ አንድ አንድ ተጫዋቾችን አስመርጠዋል።
ከቅዱስ ጊዮርጊስ አሉላ ግርማ፣ አበባው ቡጣቆ፣ ሳላዲን በርጌቾ፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ፣ ምንተስኖት አዳነ፣ አንዳርጋቸው ረታ፣ አዳነ ግርማ፣ ምንያህል ተሾመ፣ በሀይሉ አሰፋ/ቱሳ/፣ ዑመድ ኡክሪ እና ፍፁም ገብረማርያም በቡድኑ ተካተዋል።
ከደደቢት እግር ኳስ ክለብ  ሲሳይ ባንጫ፣ ታሪኩ ጌትነት፣ ስዩም ተስፋዬ፣ ብርሀኑ ቦጋለ/ፋዲጋ/፣ አክሊሉ አየነው፣ ታደለ መንገሻ፣ ዳዊት ፍቃዱ እና ሽመክት ጉግሳ ተመርጠዋል።
ከቡና ስፖርት ክለብ ጀማል ጣሰው፣ ሮቤል ግርማ፣ ቶክ ጀምስ፣ ጋቶች ቻኖም፣ መሱድ መሀመድ፣ ዳዊት እስጢፋኖስ፣ ኤፍሬም አሻሞ እና አስቻለው ግርማ ይገኙበታል ።
ከሀዋሳ ከነማ ግርማ በቀለና ታፈሰ ሰለሞን ሲመረጡ ከመከላከያ ሽመልስ ተገኝ፣ ከናሽናል ሲሚንቶ ማታይ ሉል፣ ከሙገር ሲሚንቶ አሰግድ ሽፈራው፣ ከዳሽን ቢራ ደግሞ አስራት መገርሳ ተመርጠዋል።
በውጭ አገራት ከሚጫወቱት ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች መካከል ሳላዲን ሰይድ፣ አዲስ ህንጻ፣ ጌታነህ ከበደ፣ ፍቅሩ ተፈራና ሽመልስ በቀለ ይገኙበታል።
ለሞሮኮው የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት የተመረጡት እነዚህ ተጫዋቾች ከመጪው ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ልምምድ ይጀምራሉ።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር