ሲኣን/ መድረክ የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ነው

ሲኣን/ መድረክ በዚህ ሳምንት በሃዋሳ ከተማ ለማካሄድ ላቀደው ሰላማዊ ስልፍ የጸጥታ ኃይል እንዲመደብለት ለከተማው ኣስተዳደር ላቀረበው ጥያቄ እስከኣሁን ምላሻ ኣለማግኘቱ ታውቋል።
ሪፖተራችን ጥቻ ወራና ከሃዋሳ እንደዘገበው፤ ከሳምንታት በፊት በወቅታዊ ፖለቲካዊ፤ ማህባራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን መንግስትን በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ የጸጥታ ጥበቃ እንዲደረግለት በጽሁፍ ጠይቆ የከተማዋን ኣስተዳደር ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ነው።

እንደዘጋባው ከሆነ፤ ምንም እንኳን ከከተማው ኣስተዳደር ምላሽ ባይኖረም የሰላማዊ ሰልፉ ኣዘጋጅ ኮሚቴ ለሰማላዊ ሰልፉ የሚያደርገውን ዝግጅት ኣጠናክሮ መቀጠሉ ታውቋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር