ሲዳማ ቡና ከአርባ ምንጭ ከነማ ባዶ ለባዶ ተለያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በ22ተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና እና ንግድ ባንክ ድል ቀንቷቸዋል።
ንግድ ናንክ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ነው ኢትዮጵያ መድህንን 2 ለ 0 የረታው።
በክልል ከተሞች ዳሸን ቢራ ከወላይታ ዲቻ ፣  አርባ ምንጭ ከነማ ከሲዳማ ቡና በተመሳሳይ 0 ለ 0 ሲለያዩ ፤ ሙገር ሲሚንቶ በመብራት ሃይል 2 ለ 1 ተሸንፏል።
በሌላ ጨዋታ ወደ ሀረር ያቀናው ኢትዮጵያ ቡና ሀረር ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ደደቢት ግጥሚያ 3 ለ 3 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር