ኢትዮጵያ ውስጥ ከ100 ሺሕ ሰዎች መካከል 210 ያህሉ በቲቢ ይያዛሉ ተብሎ ይገመታል

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የቲቢ ጫና አለባት ተባለ

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የቲቢ ጫና ካለባቸው አገሮች መካከል ተጠቃሽ መሆኗን በዩኤስኤድ (የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድዖ ድርጅት) ድጋፍ የሚንቀሳቀሰው የግሉ ጤና ዘርፍ ፕሮግራም ያወጣው መረጃ አመለከተ፡፡ 
መረጃው የዓለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አ. በ2013 ያወጣውን ሪፖርት ጠቅሶ እንደዘገበው ከ80 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ ውስጥ ከ100 ሺሕ ሰዎች መካከል 210 ያህሉ በቲቢ ይያዛሉ ተብሎ ይገመታል፡፡
189 ሺሕ የሚሆኑ ደግሞ የቲቢ በሽታ እንዳለባቸው መረጋገጡን መረጃው ጠቅሶ የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዚህ በሽታ ላይ ለመዝመት እንዲያስችለው የክልልና የወረዳ ጤና ቢሮዎችን በማስተባበር ጠንካራ የመንግሥትና የግል የጤና ባለሙያዎችን ያቀፈ ትስስር መፍጠሩን፣ ይህ ዓይነቱ ትስስር የቲቢና የኤችአይቪ ኤድስ ምርምራና ሕክምና ለማከናወን ምቹ መሆኑን አመልክቷል፡፡ 
የግሉ ጤና ዘርፍ ከ1998 ዓ.ም. ወዲህ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት የቲቢና የኤችአይቪ ኤድስ ምርምራና ሕክምና በመስጠት ተግባር ላይ ከተሰማራበት ጊዜ ጀምሮ፣ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የኤችአይቪ ኤድስ አስቸኳይ ጊዜ የዕርዳታ ዕቅድ በዩኤስኤድ በኩል የሚያበረክተው ዕርዳታ፣ ለምርመራውና ለሕክምናው የጐላ አስተዋጽኦ ማበርከቱም ተገልጿል፡፡
ምንጭ፦ www.ethiopianreporter.com  

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር