በሃዋሳ ከተማ ለኣምስተኛ ጊዜ የተካሄደው Everyone ታላቁ ሩጫ ውጤት ደርሶናል


"የጨቅላ ህፃናትን ህይወት እንታደግ" በሚል መሪ ቃል የእናቶችን ሞት ለመታደግ ታስቦ የተዘጋጀው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሃዋሳ ካሄዱ ይታወሳል
ውድድሩ በግማሽ ማራቶን፣ በሰባት ኪሎ ሜትርና በህፃናት ውድድር በአንድ ነጥብ ሁለት ኪሎ ሜትር ተካሂዷል።
ትናንት በተካሄደው ሩጫ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ፣ አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ፣ አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ እና ሌሎችም ታዋቂ ሰዎች  ተገኝተዋል።
በወንዶች ግማሽ ማራቶን ጤናው በለጠ  አንደኛ ሲሆን ርቀቱን ለማጠናቀቅ 1 ሰዓት ከ3 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ ወስዶበታል።
ሀብታሙ ካሳሁን 1 ሰዓት ከ 3 ደቂቃ ከ 45 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በሁለተኝነት አጠናቋል።
ሀብታሙ ካሳሁን ውድድሩን ለማጠናቀቅ በግማሽ ማራቶን ሶስተኛ የሆነው የፍቃዱ ግርማ ሲሆን ከሀብታሙ በ10 ሴኮንድ ዘግይቶ ገብቷል።
በሴቶቹ የግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር የውብዳር ተሾመ ውድድሯን በአንደኝነት ስታጠናቅቅ የወሰደባት ሰዓትም 1 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ43 ሴኮንድ ነው።
እምሻው ንጉሴ በሁለት ሴኮንድ በየውብዳር ተቀድማ ሁለተኛ ሆና ውድድሯን አጠናቃለች።
በሴቶች ግማሽ ማራቶን ሶሰተኛ የሆነችው ኑሪት ሽመልስ ስትሆን የወሰደባት ሰዓትም 1 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ15 ሴኮንድ ወስዶባታል።
በሀዋሳ ከተማ ታላቁ ሩጫ ሲካሄድ ዘንድሮ ለአምስተኛ ጊዜ ነው።
በዚህ ውድድር አሸናፊዋች በአጠቃላይ 64 ሺህ ሁለት መቶ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በሴትም በወንድም አንደኛ ሆነው ውድድራቸውን ለጨረሱ 14 ሺህ ብር ሽልማት ሲያገኙ ሁለተኛ ሆነው የጨረሱ 7 ሺህ ብር ተሸልመዋል፡፡
ሶስተኛ የወጡት ደግሞ 4 ሺህ ብር ተሸልመዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር