ሲኣን/ መድረክ በኣዲስቷ ሲዳማ ታሪክ ልዩ ቦታ ያለው የሎቄ ሰማዕታት ቀን በኣዲስ ኣበባ እና ሃዋሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ለማሰብ መዘጋጀቱ ተሰማ



የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ/ መድረክ በኣዲስቷ ሲዳማ ታሪክ ልዩ ቦታ ያለው 12ኛውን የሎቄ ሰማዕታት ቀን በኣዲስ ኣበባ እና በሃዋሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ለማሰብ መዘጋጀቱ ታውቋል።

ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ከሃዋሳ እንደዘገበው፤ የሲዳማ ልዑላዊ ግዛት መደፈርን በተቃዎሙ እና የመልካም ኣስተዳደር ጥያቄን ባነገቡ ንጽሃን ሲዳማውያን ላይ ከ12 ኣመታት በፊት ግንቦት ቀን 16 የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በግፍ በፈጸሙት የጅምላ ግዲያ ህይወታቸውን ያጡትን የሲዳማ ሰማዕታትን ለማሰብ ዝግጅት በማድረግ ላይ ነው።

የመታሰቢያው ሰነስርኣቱ በኣገር ኣቀፍ ደረጃ እና በሃዋሳ ከተማ ለማካሄድ የታሰበ ሲሆን፤ ግንቦት 16 በኣዲስ ኣበባ ከተማ በኣንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ/ መድረክ ኣዘጋጅነት በተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሲኣን በተወካዮቹ ኣማከይነት በሰልፉ ላይ በመገኘት የሎቄ ጥቃት ሰለባዎችን እንደሚያስታውስ ታውቋል።

ከዚህም በተጨማር የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ በእለቱ ማለትም ግንቦት ቀን16 በሃዋሳ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የከተማዋን ኣስተዳደር በጽሁፍ የጠየቀ ሲሆን፤ የከተማ ኣስተዳደሩን ምላሽ በመጠባበቅ ላይ መሆኑ ዘጋባው ያመለክታል።


የሎቄ ሰማዕታት ቀን በኣዲስቷ ሲዳማ ታሪክ ካለው ፋይዳ የተነሳ እለቱን በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ለማክበር የሲኣን ኣመራሮች መወሰናቸውን ተከትሎ፤ የዝግጅቱ ኣስተባባር ኮሚቴዎች ተመርጠው ወደ ስራ መግባታቸውን ጥቻ ወራና ዘግቧል። 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር