መድረክ ፓርቲ በአዲስ አበባ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

ምንጭ፦ ሬዲዮ ፋና 
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፓርቲ ዛሬ በአዲስ አበባ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ።
የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች መነሻቸውን ግንፍሌ ወንዝ ድልድይ ቅዱስ ማቲዎስ አንግሊካን ቤተክርስቲያን አድርገው ፥ በህንድ ኤምባሲ በመታጠፍ አቧሬ አደባባይን ፣ አድዋ ድልድይን በማቋረጥ ማጠቃለያቸውን የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 በተለምዶ ታቦት ማደሪያ እየተባለ በሚጠራው ሜዳ ላይ አድርገዋል።
ሰልፈኞቹ ኢህአዴግ ለሰላማዊ ድርድር በሩን ክፍት ያድርግ ፤ በአንድነት ኢትዮጵያን እንገነባለን ፤ የፕሬስ ነፃነት ይከበር ፤ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ይፈቱ ፤ መልካም አስተዳደር እውን ይሁን እና የውሃ ፣ መብራትና ስልክ አገልግሎቶች ይስተካከሉ የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።
በሰልፉ ማጠቃለያ ላይ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጎይቶም ፀጋዬ እና ዋና ፀሃፊው አቶ ገብሩ ገብረማሪያም ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፥ ፓርቲው ባዘጋጃቸው ወቅታዊ ጥያቄዎች ላይ ኢህአዴግ ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
በአዲስ አበባና ፊንፊኔ ዙሪያ የተዘጋጀው የጋራ ማስተር ፕላን ህዝባዊ ውይይት ተደርጎበት በህዝቡ መልካም ፈቃድ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባልም ብለዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር