ታላቁ የኢትዮጵያ ሩጫ በመጪው እሁድ በሐዋሳ ከተማ ይካሄዳል

ፎቶ http://www.photorun.net/index.php?content=photodisplay&id=1065&event=Gebrselassie_Hawasa_Resort
አዲስ አበባ ሚያዝያ 29/2006 አምስተኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ''የጨቅላ ህጻናትን ህይወት እንታደግ'' በሚል መሪ ቃል በመጪው እሁድ በሃዋሳ ይካሄዳል።
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት የማርኬቲንግና የገቢ ማሰባሰቢያ አስተባባሪ አቶ መርዕድ ዮሴፍ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ውድድሩ ከ10ሺ በላይ ሰዎችን ያሳትፋል፡፡
ጽህፈት ቤቱ ከ'ሁሉም' ዘመቻ ጋር በመተባበር በሚያዘጋጀው ሩጫ በህጻናት፣ በጤና ቡድኖችና በአትሌቶች መካከል የሰባት ኪሎ ሜትርና የግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ይደረጋል፡፡
አቶ መርዕድ እንዳሉት በሰባት ኪሎ ሜትሩ ውድድር ከ10ሺ በላይ የጤና ቡድኖችና 750 ህጻናት ይሳተፉበታል።
በሩጫው 120 የክለብ አትሌቶች ሲሳተፉ ከአንድ እስከ ሶስት ለሚወጡ አትሌቶች የ14፣ የሰባትና የአራት ሺህ ብር ሽልማት ይበረከታል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር