ኤጀንሲው የብሄራዊ ፈተና ጥያቄዎችን ማስቀመጥ የሚያስችል የጥያቄ ባንክ ሊያዘጋጅ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 8 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ የብሄራዊ ፈተና ጥያቄዎችን አስቀድሞ በማዘጋጀት ለማስቀመጥ የሚያስችል የጥያቄ ባንክ ሊያዘጋጅ ነው።
የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን ዱሬሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ፤ የጥያቄ ባንኩ ኤጀንሲው በማንኛውም ጊዜ በየትኛውም የትምህረት አይነት በርካታ ዝግጁ የሆኑ ጥያቄዎች እንዲኖሩት የሚያስችለው ነው።
ይህ ደግሞ በየአመቱ ለጥያቄዎች ዝግጅት የሚያስፈልገውን የሰው ሃይልና ወጪ ለመቆጠብ ያስችላል።
በተጨማሪም በማንኛውም ጊዜ ብሄራዊ ፈተናን መስጠት ቢያስፈልግ ኤጀንሲው ዝግጁ ሆኖ እንዲገኝ ያግዘዋል።
የጥያቄ ባንኩ በስራ ላይ ሲውልም በአንድ የትምህርት አይነት እስከ 5 ሺህ የሚደርሱ ተቀማጭ ጥያቄዎች ኤጀንሲው እንዲኖሩት ያስችለዋል ነው ያሉት አቶ ዘሪሁን ።
በርካታ ያደጉ ሀገራት አሰራሩን ለረጅም አመታት የተጠቀሙበት ሲሆን በኢትዮጵያም ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆናቸውንም ነው የገለጹት።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር