የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀመረ መልካም እድል ለሲዳማ ተማሪዎች!
ምንጭ፦ www.fanabc.com
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የ2ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ዛሬ በመላ ሀገሪቱ መሰጠት ጀመረ።
ፈተናውን 887 ሺህ 982 ተማሪዎች የወሰዱ ሲሆን ፥ ተማሪዎቹ በዛሬው የፈተና መርሃ ግብራቸው አማርኛ ፣ እንግሊዘኛና ሂሳብ ትምህርቶችን መፈተናቸውን ነው የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የተናገረው።
በተዘጋጁት 1 ሺህ 494 የመፈተኛ ጣቢያዎች ውስጥም ያለምንም የዲሲፕሊን ጉድለት የመጀመሪያው ቀን የፈተና ሂደት መከናወኑን የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን ዱሬሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
የሁለተኛው ቀን ፈተናም ሀሙስ ግንቦት 21 የሚቀጥል ሲሆን ፥ በሚቀጥሉት የፈተና ቀናት ውስጥም ህብረተሰቡና በፈተናው የተሳተፉ አካላት በዛሬው እለት ለፈተናው በሰላም መከናወን ያደረጉትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የፊታችን ሰኞ ደግሞ ከ199 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚፈተኑት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ይቀጥላል።
Comments
Post a Comment